ሃዋሳ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመት



ከወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ)
እንደመነሻ
“አዳራሽ ተቀምጣ ስታበላ ሥጋ ስታጠጣ ጠጅ 
ስዕል ትመስላለች የምኒሊክ ልጅ” 
 
    እንዲህ ሆነ፡- 
ዕለተ እሁድ መስከረም 27 ቀን 2005 ዓ.ም ረፋዱ ላይ ድንገት ብድግ ብዬ ወደ ሃዋሳ መረሽኩ፡፡ የሁለት ቅን እና ትንታግ ወጣቶች (መስከረም እና ፍፁም) ደግነት ነው ወደ ሃዋሣ ያንደረደረኝ፡፡ የእንዳልክና የፀሃይም ደግነት የጉድ ነው፡፡

እነሆ ሃዋሳን ለሁለተኛ ጊዜ ረገጥኳት፡፡ ድንቅ ከተማ ናት፡፡ አውራጎዳናዎቿ የተወለወሉ ይመስላሉ፡፡ አንድ ወጥ የሆነ መልክና ፋት አላቸው፡፡ እንደእኔ ዓይነቱን አልፎሂያጅ መንገደኛ “ሊያምታቱ” ይችላሉ፡፡ አቀያየሳቸውም አነጣጠፋቸውም ፍፁም ተመሳሳይ ለሆነ ወደሌላ ቦታ መሄድ ያሰበ ሰው ተጉዞ ተጉዞ ራሱን እዚያው የተነሳበት ቦታ ሊያገኘው ይችላል፡፡ ስለዚህ ከከተማዋ አንድ ጥግ ወደሌላ ጥግ መሄድ የፈለገ ሰው፣ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ቆም ብሎ እንደአሸን እየፈሉ ካሉት ትልልቅ ሕንፃዎች መሃል አንዱን በምልክትነት ማስተዋል አለበት፡፡ የሃዋሣ መንገዶች ፍፁማዊ አንድወጥነት አስገርሞኝ ዋዘኛ ጥያቄ የሰነዘርኩለት ወዳጄ “ሃዋሣ አዙሪት ነገር አለባት የሚባለው ለዚህ ነው” የሚል ምላሽ ነበር የሰጠኝ፡፡ የሆኖ ሆኖ ሃዋሳ አ/አበባን የምትስንቅ ፅዱና ውብ ከተማ ናት፡፡
ሙሉ ጽሁፉን እዚህ ላይ ያንቡ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር