አውስትራሊያ ለኢትዮጵያ የትምህርት ድጋፍ ታደርጋለች፤ የሲዳማ ልጆች የእድሉ ተጠቃሚ ሁኑ



አዲስ አበባ (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ በመተግበር ላይ ያለችውን የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ አውስትራሊያ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች፡፡
በኢትዮጵያ የአገሪቱ አምባሳደር ሊዛ ፊሊፔቶ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ የጀመረችውን ፈጣን ልማት ማስቀጠል የሚችል ብቃት ያለው የሰው ኃይል በማሰልጠን በኩል አገራቸው ቁርጠኛ አቋም አላት፡፡
በተለይ ኢትዮጵያ በአምስት ዓመቱ ሀገራዊ ዕቅዷ ከፍተኛ ትኩረት ከሰጠቻቸው መካከል ትምህርት፣ ግብርና እና የምግብ ዋስትና መረጋገጥ እንዲሁም በጤናው ዘርፍ አቅሟን ለመገንባት አውስትራሊያ ዝግጁ መሆኗን አምባሳደሯ ገልጸዋል፡፡
አውስትራሊያ በማዕድንና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እንዲሁም በውሃና በንጽህና አጠባበቅ ያላትን ልምድና የቴክኖሎጂ አቅም ተጠቅማ በመስኩ የኢትዮጵያን የሰው ኃይል አቅም ለማሳደግ ትሰራለች ብለዋል፡፡
አውስትራሊያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2014 ጀምሮ ለአፍሪካ
ሀገራት እንደ የማስትሬትና ዶክትሬት ዲግሪ ነፃ የትምህርት ዕድል መስጠት የሚያስችላትን የምዝገባ መርሐ ግብር ከመስከረም ወር ጀምሮ እስከ መጪው ታኅሣሥ ወር ድረስ ክፍት ማድረጓን አስታ ውቃለች፡፡
በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ የልማት ትብብር ኮርፖሬሽን ኃላፊ ፒተር ደንካን ጆንስ በበኩላቸው እንዳሉት የትምህርት ዕድሉ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች አቅም ከማጎልበት ባሻገር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነው፡፡
የአውስትራሊያ መንግሥት የሰጠው ይኸው የትምህርት ዕድል ኢትዮጵያ ቅድሚያ ትኩረት በሰጠቻቸው የልማት መስኮች እንዲሆኑ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ምክክር የተደረገበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የሥልጠናው ትኩረትም በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና እና የምግብ ዋስትና፣ ባቡርና ምህንድስና ጨምሮ በተለያዩ የመሠረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ፣ በማዕድንና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠናዎች መስኮች መሆኑን ኃላፊው አመልክተዋል፡፡ 
ለ2014 በተጀመረው ነፃ የትምህርት ዕድል ምዝገባ ላይም ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች በንቃት በመሳተፍ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ለመመዝገብ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾችም በwww.adsafrica.com.au ድረ-ገጽ መመዝገብ እንደሚችሉ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ 
አውስትራሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የልማት ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ከሁለት ዓመት በፊት የልማት ትብብር ኮርፖሬሽን ቢሮ አዲስ አበባ ውስጥ መክፈቷ የሚታወስ ነው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር