የፌደራል የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ በሀዋሣ ከተማ ለሚገኙ የጡረተኞች ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡


ኤጀንሲው ድጋፉን ያደረገው ከሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትርና ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በመተባበር መሆኑም ታውቋል፡፡
በኤጀንሲው የሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ራሄል ዘውዴ እንዳሉት የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ህፃናት የነገ ሀገር ተረካቢ መሆናቸውን በውል በመረዳት ከልዩ ልዩ አካላት ስፖርንሰር በማፈላለግ ልዩ ልዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው 169 በሞግዚት የሚተዳደሩ ህፃናት መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
ለህፃናቱ የዚህን አይነት ድጋፍ ማድረግ ትምህርታቸውን በሚገባ እንዲከታተሉ አስተዋፅኦው የጐላ መሆኑም ተናግረዋል ሲል የዘገባው በኃይሉ ጌታቸው ነው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/30MesTextN805.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር