የሐዋሳ-ሀገረማሪያም የአስፋልት መንገድ ግንባታን ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው


አዲስ አበባ፣መስከረም 21/2005/ዋኢማ/-የአራተኛው የመንገድ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም አካል የሆነውና የ198 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የሐዋሳ-ሀገረማሪያም የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታን ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።

ግንባታው ወደ ሦስት ቢሊየን ብር ይፈጃል ተብሎ የሚጠበቀው ይኸው የመንገድ ፕሮጄክት የትራንስ አፍሪካን ሃይዌይ መንገድ አካልና የኬንያን ሞምባሳ ወደብ ከአዲስ አበባ ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ ነው።

የመንገዱ መገንባት በኢትዮጵያና ኬንያ መካከል ያለውን የንግድና የትራንስፖርት ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ተናግረዋል።

ለዚህ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ማስፈጸሚያ የሚውለውን ወጭ የሚሸፍነው የአፍሪካ ልማት ባንክ መሆኑን አቶ ሳምሶን ተናግረዋል።

http://www.waltainfo.com/index.php?option=com_content&view=article&id=5457:2012-10-01-13-54-37&catid=58:2011-08-29-12-55-21&Itemid=383

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር