አምባሳደር ብርሃነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊሆኑ ነው


የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ሞት ተከትሎ በተጠራው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ ምክትላቸው የነበሩትን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ከሾመ ወዲህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱ ቦታ ክፍት ሆኖ የቆየ ሲሆን ለዚህም ሚኒስቴሩን ላለፉት ሁለት አመታት በሚኒስትር ደኤታነት ያገለገሉት አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ እንደታጩ መመደባቸውን ምንጮቻችን አመለከቱ፡፡ ሀገሪቱ የምትመራበትን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በማርቀቅ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው አምባሳደር ብርሃነ፤ ከሚኒስትር ደኤታነታቸው በፊት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአምስት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን የተጓተቱ እቅዶችን ጨምሮ በተያዘለት ጊዜ ለማስፈፀም እንዲቻል በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራና ባለ ድርሻ ባለሙያዎች የተካተቱበት ግብረሃይል ተቋቋመ፡፡
በተያያዘም አቶ ኃይለማርያም በቦርድ ሰብሳቢነት ይመሩት የነበረው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ድሪባ ኩማ መሠጠቱንና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን በቅርቡ እንደሚቋቋም ምንጮቹ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
 http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=2944:%E1%8A%A0%E1%88%9D%E1%89%A3%E1%88%B3%E1%8B%B0%E1%88%AD-%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%88%83%E1%8A%90-%E1%8B%A8%E1%8B%8D%E1%8C%AD-%E1%8C%89%E1%8B%B3%E1%8B%AD-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AD-%E1%88%8A%E1%88%86%E1%8A%91-%E1%8A%90%E1%8B%8D&Itemid=20

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር