የቴዲ አፍሮ የሐዋሳ ኮንሰርት ለሳምንት ተላለፈ



ስቴዲየሙ ለጨዋታ ተፈልጓል
በዛሬው ዕለት በሐዋሳ ከተማ ሊደረግ ታቅዶ የነበረው የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ኮንሰርት ስቴዲየሙ ለኳስ ጨዋታ በመፈለጉ ተሰርዞ ለሚቀጥለው ቅዳሜ ተላለፈ፡፡ የቤለማ ኢንተርቴይመንት የፕሮሞሽን እና ኢቬንት ሐላፊ አቶ ምኞት ኃይሉ (ዲጄ ዊሽ) ለአዲስ አድማስ እንደገለፀው፤ ቤለማ ኢንተርቴይመንት በዛሬው ዕለት በሐዋሳ ከተማ ትልቅ የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ አስቦ ዝግጅቱን ካጠናቀቀ በኋላ ኮንሰርቱ ሊደረግበት የታቀደው ስታዲየም ለኳስ ጨዋታ ይፈለጋል በመባሉ ዝግጅቱ ለጥቅምት 24 ቀን 2005 ዓ.ም ሊተላለፍ ችሏል፡፡
ዝግጅቱ በዕለቱ ሊደረግ ከታቀደ በኋላ ለፕሪሚየር ሊግ ዕጣ ሲወጣ የሐዋሳ ከነማ እና የመድሕን ጨዋታ ጥቅምት 17 ቀን 2004 ዓ.ም በሐዋሳ ስታዲየም ስለወጣላቸው ኮንሰርቱ ሊተላለፍ እንደቻለ ታውቋል፡፡
የዝግጅቱ ቀን በመተላለፉ ለማስታወቂያ ከወጣው 42 ሺህ ብር ውጭ ምንም ዓይነት ኪሣራ አለመድረሱን የገለፀው ዲጄ ዊሽ፤ በቀኑ መተላለፍ ምክንያት ተፈጥሮ የነበረው ትልቅ ስጋት የአርቲስት ቴዲ አፍሮን ፕሮግራም አለማወቃቸው መሆኑን ጠቁሞ፤ ሆኖም አርቲስቱ እና ዛየን ባንድ ትልቅ ትብብር እንዳደረጉላቸው ገልጿል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር