የሞዴል ትምህርት ቤቶችን ቁጥር በማበራከት በትምህርት ተደራሽነት ላይ የተገኘውን ውጤት በትምህርት ጥራትም ላይ ለመድገም እየሠራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የማልጋ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡



ጽህፈት ቤቱ በወረዳው 6ቱንም የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆችንና ሌሎች ተጨማሪ ተግባራትን በአግባቡ በማከናወን የሞዴልነት ማዕከል የሆነው የማልጋ የመጀመሪያ ሳይክል 1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ተሞክሮን ሌሎችም እንዲቀስሙ የልምድ ልውውጥ ኘሮግራም አካሂዷል፡፡
በዚህም ወቅት የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሻለ ሻላሞ እንዳሉት ጥራቱ በተጠበቀ ትምህርት የተቀረፀ ዜጋና የልማት ሠራዊት ለማፍራት በወረዳው የተጠናከረ ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡
በዚህም መሠረት በ2ዐዐ4 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑት ከ86ዐ በላይ ተማዎች 9ዐ በመቶ በላይ የሚሆኑ ፈተናውን ማለፋቸውንና ይህም ከቀደሙት ዓመታት 49 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን አስረድተዋል፡፡
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አየለ አላካ በበኩላቸው በተገኘውን ውጤት አጠናክረን ካስቀጠልን በታላቁና በባለራዕዩ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የተነደፈውን የትምህርት ፖሊሲ አጭር መንገድ ተጉዘን እናሳካለን ብለዋል፡፡

በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ተስፋሁን በየነ 2ዐ የ1 ለ5 አደረጃጀቶችን በመጠቀም ውጤታማ ሥራ መሥራቱን ገልፀው ተማሪዎችም ኩረጃን ሙሉ በሙሉ እንዲፀየፉ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ቤቱ ላስመዘገበው ውጤት የላቀ ድርሻ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የምስክር ወረቀት መስጠቱንና የትምህርት ቤቱ እሴቱ የሆኑ ምርጥ ተሞክሮዎች በታዳሚዎች መጎብኘቱን የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/16MesTextN405.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር