በሲዳማ ዞን በይርጋለም ከተማ የኤች አይ ቪ ኤድስን ስርጭት ለመግታት በህብረተሰቡ በየጊዜው በተሠጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት የአመለካከት ለውጥ ማሳየቱ ተገለፀ፡፡

በይርጋለም ከተማ ቤዛ የወጣቶች ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞላልኝ ሀያሉ ማዕከሉ በዋናነት ትኩረት አድርጎ የሚሠሩት በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ዙሪያ በኤች አይ ቪ ኤድስ እንዲሁም ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ነፍሰጡር እናቶችና ህፃናት ላይ መሆኑን ጠቅሰው ወጣቶች ለኤድስ ተጋላጭ የሚሆኑት ምቹ የመዋያ አካባቢ ባለመኖሩ ነው ብለዋል፡፡

በቤዛ የወጣቶች ማዕከል ቫይረሱ በደማቸው የሚገኙ ህፃናትና ነፍሰጡር እናቶች አስተባባሪ ወዘሪት ልሳነወርቅ ተስፋዬ በበኩላቸው ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ወገኖች ቁጥር በአሁኑ ጊዜ 32 መድረሱን ገልፀው ሁሉም የማህበሩ አባላት እንደየአቅማቸው በመቆጠብ የኢኮኖሚ አቅማቸውን እያሳደጉ እንደሚገኙ አስታውቃለች፡፡
በቤዛ ወጣቶች ማዕከል የቡና ጠጡ ኘሮግራም አዘጋጅና አሳታፊ ወይዘሮ ጥሩነሽ ፀጋዬ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ያለባቸው ወገኖችን ማቅረብና የመድሀኒት አጠቃቀማቸውን መከታተል ተገቢ  መሆኑን ገልፀው በማህበር ያልተደራጁ ወደ ማህበሩ መጥተው ተገቢውን ድጋፍና እርዳታ እንዲያገኙ አስገንዝበዋል፡፡ አዳነ አለማየሁ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ እንደዘገበው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/25MesTextN605.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር