ተቃዋሚዎች የምርጫው ሜዳ መስተካከል አለበት አሉ


በመጪው ሚያዚያ ወር በሚደረገው የአካባቢ ምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ ላይ ምርጫ ቦርድ ከ75 ፓርቲዎች ጋ ከትላንት በስቲያ የመከረ ሲሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከጊዜ ሰሌዳው በፊት መቅደም ያሉባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ገለፁ፡፡የምርጫ አጃቢና አሯሯጭ መሆን ስለማንፈልግ የምርጫው ሜዳ መስተካከል አለበት ብለዋል - ተቃዋሚ ፓርቲዎች፡፡ሃያ አንድ ነጥቦችን ባካተተው የምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የአንድነት ፓርቲ ሃላፊ አቶ አስራት ጣሴ፤ የፖለቲካ ምህዳሩ በተጣበበበትና የፕሬስ ነፃነት በሌለበት ሁኔታ ነፃ፣ ግልጽና ፍትሃዊ ምርጫ ማድረግ የማይታሰብ ነው ብለዋል፡፡ ወደ ጊዜ ሰሌዳ ውይይት ከመገባቱ በፊት የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት እንዳለበትም ገልፀዋል፡፡
ከህዳር 17 ጀምሮ የወረዳ የምርጫ ጽ/ቤቶች ተከፍተው ስራ እንደሚጀምሩና ሚያዚያ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ምርጫው እንደሚደረግ የጠቀሱት አቶ አስራት፤ ከጊዜ ሰሌዳ በፊት መቅደም ያሉባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ጠቁመው፤ አጃቢ እና አሯሯጭ ሳይሆን ነፃ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ምርጫ ላይ መሳተፍ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩ ከሰፋና ሌሎች ችግሮች ከተፈቱ አንድነትና መድረክ በአካባቢ ምርጫ እንደሚሳተፉ ገልፀዋል፡፡
የኢዴፓ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ወንድወሰን ተሾመ በበኩላቸው፤ ከጊዜ ሰሌዳው በፊት የምርጫው ሜዳ መስተካከል አለበት ብለዋል - “የመራጮች ምዝገባ እና የፓርቲዎቹ የምርጫ ክርክር ጊዜ የተጣጣመ አይደለም” በማለት፡፡ ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ ያሉትን ችግሮች አጽድቶ የተመቻቸ የምርጫ ሜዳ እንዲፈጠር ጠይቀዋል - አቶ ወንድወሰን፡፡
http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=3019:%E1%89%B0%E1%89%83%E1%8B%8B%E1%88%9A%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%8B%A8%E1%88%9D%E1%88%AD%E1%8C%AB%E1%8B%8D-%E1%88%9C%E1%8B%B3-%E1%88%98%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8A%AB%E1%8A%A8%E1%88%8D-%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%89%A0%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%88%89&Itemid=20

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር