የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የማስፈፀም አቅሙን ከፍ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡



የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የማስፈፀም አቅሙን ከፍ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በ2ዐዐ4 በጀት አመት በከተማ አስተዳደሩ የተሻለ አፈፃፀም ካስመዘገቡ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የአገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽ ለማድረግና የተሻሻሉ አሰራሮች ተግባራዊ እንዲሆኑ እስከታችኛው የመስሪያ ቤቱ መዋቅር ድረስ ሂስና ግለሂስ አድርጓል፡፡
በግምገማው ወቅት እንደተጠቆመው ማዘጋጃ ቤት በባህሪው አገልግሎት ሰጪ ተቋም አንደመሆኑ መጠን በሰራተኛው የአመለካከት ችግርና የክህሎት ክፍተት ምክንያት ሙሉ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት አልተቻለም፡፡
እንደ አቶ ዮናስ ዮሴፍ የሀዋሣ ከተማ ከንቲባ ገለፃ ከከተማ ልማት ስራዎቻችን መካከል ተጠቃሹ የከተማ ነዋሪውን የአገልግሎት ፍላጎቶች ተደራሽ ማድረግ ሲሆን ለዚህም የሲቪል ሰርቫንቱን የአፈፃፀም አቅምና አመለካከቱ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው ብለዋል፡፡

አቶ ብሩ ወልዴ የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች ዋና ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው ምንም እንኳን ባለፈው በጀት አመት ማዘጋጃ ቤቱ በተለያዩ የሀገርና ክልል አቀፍ መድረኮች ተሸላሚ ያደረጉትን ስራዎች እንደሰራ ቢታወቅም ይህ ማለት ግን የአገልግሎት አሰጣጡ ሙሉ ነው ማለት አይደለም፡፡
ስለሆነም ያለብንን የአሰራር ክፍተቶች እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በመገምገም የተሸለ አፈፃፀም እንዲኖረን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
ማዘጋጃ ቤቱ ከዚህ ጐን ለጎን በ2ዐዐ4 በጀት አመት በአገልግሎት አሰጣጣቸው፣ በመረጃ አያያዛቸውና ከዋናው ማዘጋጃ ቤት ጋር ባላቸው የአሰራር ግልፀኝነት በከተማዋ ከሚገኙ 8 ክፍለ ከተሞች የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማን አንደኛ የመናኸሪያ ክፍለ ከተማን ሁለተኛ እንዲሁም የታቦር ክፍለ ከተማን ሶስተኛ አድርጐ ሸልሟል፡፡የከተማው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/30MesTextN105.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር