ሰሞኑን በመንግስት መገናኛ ብዙሃን የሲዳማ ክልል ጥያቄን እና የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደርን በተመለከተው በሲዳማ ኣመራር ስም በተሰጠው የኣቋም መግለጫ ኣብዛኛዎቹ ኣመራሮች ማዘናቸው ተገለጸ


ከኣመራር ኣባላቱ መካከል ስማቸው እንዲገለጸ ያልፈለጉት ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያሉት የሲዳማ ኣመራሮች ኣሳላፉ ተብሎው በመንግስት መገናኛ ብዙሃን የተሰራጨም የኣቋም መግለጫ የብዙዎቹን ኣመራር ኣቋም የማያንጸባርቅ እና በብዙሃኑ የሲዳማ ኣመራር ስም ጥቂቶች የግል ፖለቲካ ማስፈጸሚያነት ያስተላለፉት የ ኣቋም መግለጫ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰሞኑን በሲዳማ ክልል ጥያቄ እና በሃዋሳ ከተማ ኣሰተዳደር የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ ብሎም የኣመራር ኣባላቱን ኣቋም በገመገመበት በዚህ ወቅት፤ የሲዳማ ክልል ጥያቄ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ኣይደለም ካለመባሉ በላይ የክልል ጥያቄውን ያነሱ ኣካላት ጸረ ሲዳማ ናቸው ሲዳማን ኣይወክሉም ኣልተባለም ብለዋል።

ምንም እንኳን መድረኩን ይመሩ የነበሩት የኣመራሩ ኣባላት በሲዳማ ክልል ጥያቄ ላይ ኣሉታዊ ኣመለካከት እንዲያዝ ከፍተኛ ግፊት ያደረጉባቸው ቢሆንም ቤቱ ግን በክልል ጥያቄ ኣስፈላጊነት ላይ የሞቀ ክርክር በማድረግ ተጋፍጧቸዋል ያሉ ሲሆን፤ በርካታ ሰኣት ከወሰደው ክርክር በኃላ የክልል ጥያቄው እንዲቆይ መስማማታቸውን እነዚሁ ኣስተያዬት ሰጪዎች ኣብራርተዋል።

የኣገሪቷ መንግስት የጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ኣቶ መለስ ዜናዊ ሞትን ተከትሎ በሽግግር ላይ የምገኝ በመሆኑ የክልል ጥያቄው ለጊዜው እንዲዘገይ ለመደረጉ እንደ ዋነኛ ምክንያትነት መነሳቱን ኣስረድተዋል።

ነገር ግን ጉባኤው ከተጠናቀቀ በኃላ በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን በተላላፈው ዜና ላይ የሲዳማ ክልል ጥያቄ ኣግባቢነት የሌለው መሆኑን እና የክልል ጥያቄውን ያነሱ ኣካላት ጸረ ሰላም ኃይሎች እንዲሁም የሲዳማን ህዝብ የማይወክሉ ተብለው መነቀፋቸው እንዳሳዘናቸው ገልጸው፤ በኣጠቃላይ የሲዳማ ኣመራር ስም በተሰጠውን ኣቋም መግለጫ ጥቅት ኣመራሮች የግል ፖለቲካ ማሳኪያነት መጠቀማቸውን ጠቅሰዋል።

ኣያይዘውም በባለዘጠኝ ነጥብ ኣቋም መግለጫው ላይ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር በስብጥር የማስተዳደሪን የተመለከተ ጉዳይ ኣንዱ መሆኑን ያስታወሱት ኣስተያየት ሰጪዎቹ፤ በኣቋም መግለጫው ላይ በጉዳዩ ዙሪያ የተነሳው ነጥብ የኣመራሮቹን ኣቋም ሙሉ በሙሉ የሚያንጸባርቅ ኣለመሆኑ ተናግረዋል።

ኣክለውም፤ የኣመራሮቹ ኣቋም የነበረው የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር በስብጥር ብትተዳደር እንደማይቃወሙ ነገር ግን ኣሁን በስራ ላይ ያለውን የከተማዋን ኣመራር ሙሉ በሙሉ እንደምቀበሉ እና ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል መስማማታቸውን የምገልጽ መሆኑን ኣመልክቷል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር