ህገ-መንግስቱ ያገሪቱ የበላይ ህግ ነው የተባለው ድንጋጌ ይከበር!!




Sidama times የዜና መጽሔት የተገኘ
ህገ-መንግስቱ ያገሪቱ የበላይ ህግ ነው የተባለው ድንጋጌ ይከበር!!
ውድ አንባቢዮቻችን እንደ ምን ሰነበታችሁ? በባለፈው ፁሑፋችን የሲዳማ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ በህገ- መንግስቱ እይታ ሲፈተሸ ምን ገፅታ እንዳለው ባጭሩ ለማስቃኘት መመኮራችን ይታወሳል፡፡ በዛሬው አጭር ፁሑፋችን የሲዳማ ህዝብ ክልል ባለማግኘቱ የተጎዳባችሁን ሁኔታዎች እንቃኛለን፡፡ መልካም መቆይታ
በቀደመው ፁሑፋችን ለማንሳት እንደሞከርነው የሲዳማ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ በቅርብ ጊዜ የተጀመረ እንዳልሆነና ለዘመናት ይህንን ጥያቄ ህዝባች ሲያነሳ የቆየ፡ ነገር ግን ህጋዊ ምላሽ ተነፍጎን እንደኖረ አይተናል፡፡
አንባገነኑ የደርግ ስርዓት እንዲዳከምና በኃላም እንዲንኮታኮት ከፍተኛ የሆነ የትጥቅ ትግል በማድረግ ለሀገሪቱ ነፃነትና ለዲሞክራሲ ማደግ ከፍተኛ ሚና የተጫወት ህዝብ ነው የሲዳማ ህዝብ፡፡ የሀገሪቱ የፖለለቲካ ምህዳር ሲቀየርና የፌደራሊዝም ስርዓት እንደብቸኛ አማራጫ ተደርጎ ሲወሰድ የሀገራችን ለየት ብሎ የጎሳ ፌደራላዊ ስርዓት ሆኖ ተዋቅሯል፡፡
ይህ የፌደራል ስርዓት ለአብዛኞዎቹ ብ//ሕ በወቅቱ አንግቦት ለነበረው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ታስቦ የተወሰደ እርምጃ ይመስላል፡፡ ይህ በጎሳ የመከፋፈል እርምጃ ከሀገሪቷ አንድነት እይታ ትክክለኛ ነው አይደለም የሚለውን አሁን አንመለከተውም፡፡ የብ//ሕ ጥያቄው ምላሽ ማግኘት አለበት ሲባልም የተለያየ እንድምታ ያለው ይሆናል፡፡ ግማሾቱ የመገንጠል ጥያቄ፣ ግማሾቹ እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ፣ ለሎቹ ደግሞ ለፖለቲካ መንበረ ስልጣን ወዘተ ጥያቄዎችን አንግበው የሚንቀሳቀሱ ነበሩ፡፡
የሲዳማም ህዝብም ያለውን የቆየ የትግል ታሪክና እምቅ አቅሙን ተጠቅሞ ቢያንስ በክልል ደረጃ ሊዋቀር ይግባል የሚል እምነት የነበነረ ቢሆንም ሳይሆን ቀረ፡፡ ይህም በመሆኑ ለበርካታ ችግሮችና እንግልቶች ልንዳረግ የግድ ሆኖዋል፡፡ የምንከተለው የጎሳ የፌዴራሊዝም ስርዓት በቋንቀቋና በጎሳ አንድ/ ተመሳሳይ የሆኑትን ህዝቦች አንድ ላይ በማደራጅት ክልሎችን መመስረት የሚል ሲሆን መበተቃራኒው እኛ ደግሞ ለጭቆና አገዛዝ ለመዳረግ በቅተና፡፡ እስቲ የሚከተለውን በዝርዝር እንመልከት፡-
  1. በመጀመሪያ ደረጃ ያጣነው ነገር ቢኖር የማንነታችን አለመከበሩና ህልውናችን መነካቱ ነው፡፡ የሲዳማ ህዝብ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር አንጋፋ ህዝብ ነው፡፡ በመልከዓ ምድር አቀማመጥም በጣም ስፋት ያለውን ደቡባዊ የሀገሪቱን ጂኦግራፊያዊ ክልልን ይሸፍናል፡፡ በሀብት ክምችትም በጣም የተደላደለ ሀገር ነው፡፡ ሰው ያጎደለብን እንጂ ተፈጥሮ ያጎደለብን ነገር የለም ይህ አንጋፋ ህዝብ ክልል መሆን ያንሰዋል እንጂ አይበዛበትም፡፡ ምክንያቱም አንድ ሉአላዊ ሀገር መሆን የሚችል ህዝብ ነውና፡፡ ይህ ህዝብ ለሌሎች አናሳ ብሔረሰቦች የተሰጠው ክልል ሳይሰጠው ቀርቶ በሀገሪቱ ውስጥ ዝቅተና ቦታና ግምት ተሰጥቶት ክብር ተነፍጎት ለመኖር ተገዷል፡፡ የሚገባንን ክብር አላገኘንም ክብር የሰው ልጅ መሰረታዊ ነገር ነው፡፡ ያለክብር መኖር አይቻልም !!
ክልል በመከልከል በሀገሪቱ ውስጥ ሊኖረን የሚችለውን የፖለቲካ ተፅኖና ቦታ በመንፈግ ክባራችንን ነክተውብናል መርዛማዎች ደህዴኖች፡፡ የሲዳማ ጠቅላይ ግዛት፡ በኃላም የሲዳማ ፣ክ/ሀገር የሚለውን ገናና ስማችንን አጥፍተው ደረጃችንና ክብራችንን በማዋረድ በህልውናች ላይ ተጫውተውብና
፡፡ ዝቅ አድርገውናል፤ አዋርደውናል፡፡ አንድ ህዝብ ክብሩንና ማንነቱን ሳያስከብር ስለሌላ ጥቅም መናገር ይከብዳል ክብር ቀዳሚ ነውና፡፡ ፈጣሪ ክቡር አድርጎ የፈጠረን ሲሆን ክልላችንን በመከልከል ክብራችንን ቀምተውናል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በቅርብ ቀን ክብራችንን ይመልሳል፡፡ አሜን!!
  1. በሁለተኛ ደረጃ ህገ- መንግስቱ ለብ// ያጎናፀፈው እራስን በራስ ለማስተዳደርና የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት አጥተናል፡፡ የራሳችንን እድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል የሚለውን የህገ-መንግስታዊ መብታችንን ተነፍገናል፡፡ ራሳችንን በራሳች መምራትና ማስተዳደር አልቻልንም፤ የኛን ጉዳይ የሚወስኑ ቁልፍና ወሳኝ ቦታዎችን የተቆጣተሩት የፀረ- ሲዳማ ህዝብ ሀይሎች በመሆናቸው ህዝባችን በባሰ ችግር ቀንበር ስር ለመውደቅ በቅቷል፡፡ በደልንና ጭቆናን በመቃወም የደም ዋጋ ከገበረ በኃላ ቀን ይወጣልኛል ብሎ ብሩህ ተስፋን ሰንቆ የታገለው ኩሩና ጀግና የሲዳማ ህዝብ ዳግመኛ በባሪያዎች ባርነት ቀንበር ስር ሊወድቅ ችሏል፡፡ ደኢህዴን የሚሊሉት ሰይጣናዊ ተልኮን ያነገበውን የፀረ-ሲዳማ ህዝብ ድርጅት የሚመሩትን የሲዳማ ጠላቶች በመሆናቸውና የሲዳማ ህዝብ ክብር እንዲነካ ሌት ተቀን የሚረባረቡ በመሆናቸው ይህንን እቅዳቸውን ለማሳካትም ያለእረፍት በመስራት ህዝባችንን በተደጋጋሚ ለታሪካዊ በደል ዳርገዋል፡፡


  1. ራሳችንን በራሳችን ብናስተዳድርና ክልል ብንሆን ኖሮ ለለሲዳማ ህዝብ ጠላት ተኩላዎች ተላልፈን አንሰጥም ነበር፡፡ የሲዳማ ህዝብ ለማዋረድ፣ ሁለመናው እንዲመናመን በመስራት ህዝባችንን የጥፋት ሴራ ቤተ-ሙከራ ያደረጉን እኮ የክልል ጥያቄያችን ባለመመለሱ ነው፡፡ እያንዳንዱ የፖሊሲ እስትራቴጂያዊ አቅጣጫ በሲዳማ ህዝብ ላይ ይሞከርና ውጤቱ ለሌሎች ይሆናል፡፡ ህዝባችንን ሌት ተቀን እያናጉ እረፍት የሚከለክሉንና እድገታችንን የሚያደናቅፉት ደኢህደኖች እኮ ክልል ባለመሆናችን ብቻ ነው፡፡ በሲዳማ ምድር ያነገሳቸውም ይህ ነውና፡፡ እኛ ክልል ብንሆን፡ እራሳችንን በራሳችን ብንመራ፡ ባህላዊ እሴቶቻችንን አካትተን ህዝባችንን የሲዳማን ንፁህ ወግና ባህል ባካተተ መልኩ ብናስተዳድር ኖሮ ሲዳማችን ከእኛም አልፎ ለሌሎች ጭምር ተስፋ መሆን ትችል ነበር፡፡
  2. በመገናኛ ብዙኸናቸው የስድብ ሰለባ ሆነናል፡፡ ደኢህደኖች መላውን የሲዳማ ህዝብ ሌቦች፣ ኪራይ ሰብሳቢዎች፣ ጠባቦች፣ ትምኪተኞች፣ ዘረኞች ወዘተ በማለት የህዝባችንን ክብርና ህልውና የሚነካ ስራ ይሰራሉ፡፡ አንድ ግለሰብ ባጠፋ ጥፋት መላውና ገናናው ህዝባችን ይሰደባል፡፡ ሲዳማን ማዋረድና ማንቋሸሽ የክልሉ ባለስልጣናት ሰይጣናዊ ቀዳማዊ ተልኮ በመሆኑ፡፡ በራሳችን ክልል ማን ይሰድበናል? የራሳችንን ድክመት አርመን ወግና መልካም ባህላችንን በመጠበቅ በክብር እንኖራለን፡፡ እነሱም የኦሮሞንና የትግራይ ክልል ህዝብ እንዳልሰደቡና እንዳልነኩ እኛም አንጀታቸው እያረረ ክልል ብንሆን ይህ ሁሉ ይቀራል፡፡
  3. ያለንን እምቅ የተፈጥሮና የሰው ሀብት በመበዝበዝ ለድህነት ዳርገውን አቅማችን በሁሉም ዘርፍ እንዲዳከም አድረገውናል፡፡ የሲዳማን ሀብት ሌሎች እንዲመዘብሩ በማድረግ ሌቦችን በመሾም፡ ለህዝብ የሚወግኑትን የሲዳማ ልጆች በማሰርና በማሳደድ እንድንደኸይ አደረጉን፡፡ ያለንን እምቅ ሀብት ተጠቅመን በእድገት ጎዳና ከመራመድ ፋንታ ሀብታችንን በመቀራመት የሲዳማን ልጆች ለረሀብ እንዲጋለጡ አድርገዋል፡፡ የሲዳማ ሀብት ተጠቃሚዎች የገዢው መደብ አባላትና ጥቂቶች ህዝብ የጣለበትን ኃላፊነት የካዱ ግለሰቦች ብቻ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ፍርድ በቀረበ ጊዜ ግን ይህ ሁሉ መስመሩን ይይዛል፡፡ ጠላታችን ደኢህዴን የሚረባረበው ሲዳማን ለማደኸየት እንጂ ህዝብን በእድገት ጎዳና ለመምራት የሚያስብና የሚያስገድድ አዕምሮ የለውም እነሱም ለመጥቀም የቆሙላቸው የተለየ ወገን ያላቸው በመሆኑ!!
  4. ባለን ሀብትና የሰው ሀይል አቅም መሰረትም በክልልና በማዕከላዊ መዋቅር ውስጥ ሊኖረን የሚገባው የህዝባችን ተወካይ አለመኖር ሌላኛው የህዝባችን ችግር ነው፡፡ ከህዝብ ብዛት በጣት የሚቆጠሩ ጎሳዎች በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እስከ 6 የሚሆኑ ሚኒስትሮችና ተወካዮች ያሏቸው ሲሆን ከ 6 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የሲዳማ ህዝብ ግን አንድ ሚኒስተር ብቻ እንዲኖረው ተደርጓል፡፡ ክልላችንን በራሳችን ብናስተዳድር ይህ ሁሉ በደል ይቆምና ተመጣጣኝ የሆነ ውክልና በማግኘት የህዝባችንን ክብር፤ ጥቅምና መብት እናስከብራለን፡፡
  5. የህዝብን ብዛትና የክልልን መንግስት መሰረት በማድረግ የሚመደበው በጀት በመቅረቱ እጅግ በጣም ለጉዳት ተዳርገናል፡፡ በልማትም ወደ ኃላ ቀርተናል፡፡ ሌሎች ክልሎች በክልልነታቸው በጀት ሲመደብላቸው እኛ ግን ለአንድ ክልል የሚመደበውን በጀት ከ56 //ህዝብ ጋር ለመጋራት ተገደናል፡፡ ይህ ደግሞ ከቆዳ ስፋታችን፣ በመሰረተ ልማት ወደ ኃላ የቀረን በመሆናችን፣ ከህዝብ ቁጥር ብዛታችን… ወዘተ ሲታይ በጣም ዝቅተኛ ይሆናል፡፡ አምስቱ ክልሎች በአንድነት ተደምረው የሲዳማን ህዝብ ብዛት የማይደርሱ ሲሆን ነገር ግን እነዚህ ክልሎች በክልል ደረጃ በጀት ይመደብላቸዋል፤ እኛ ግን ይህ ሁሉ አቅምና ተዛማጅ ችግሮች ያሉብን ቢሆንም ምንም እየተጠቀምን አይደለንም፡፡
  6. በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ የራሳችን መገናኛ ብዙሀን ቻናል ካለመኖሩ የተነሳ ህዝባችን ማንነቱን ባህሉንና ወጉን ለማሳደግና ለሌሎች እንዲታወቅ ማድረግ አልተቻለም፡፡ ሌሎች ክልሎች የራሳቸው የሆነ የሬዲዮና የቴሌብዥን ጣቢያ ያላቸው ሲሆን የሲዳማ ብሐር ማንነት በአመት አንዴ እንኳን በሚዲያ አይተላለፍም፡፡ በክልልና በሀገር አቀፍ ሚዲያም ቢሆን የሲዳምኛ ሙዚቃ በአመት አንዴም አይጋበዝም፡፡


የተወደዳችሁ ወገኖቻችንን፡ በእኛ ላይ እየደረሰብን ያለውን በደልንና ጭቆናን በዚህ አጭር ፁሑፍ ዘርዝሮ መጨረስ እጅግ በጣም ይከብዳል፡፡ ከላይ ያነሳናቸውንና ሌሎችንም ጉዳዮችንም ብንመለከት በእውኑ አልተጎዳንም አልተረገጥንም ትላላችሁን??
እስቲ አሁን ደግሞ ክልል በመሆናችን የምንጎናፀፋቸውን ጥቅሞች በአጭሩ እንመለከታለን
  1. ከምንም ከምንም በላይ ስማችንንና ክብራችን እንዲጠበቅልን ይረዳናል፡፡ የሲዳማ ህዝብ ኩሩና ክብር ህዝብ እንደሆነ ዳግመኛ ማሳየት፡፡ራሳችንን በራሳችን አስተዳድረን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብታችን ተጠቅመን የራሳችንን ክልል ሆነን በራሳችን ክልል ከብረን እንኖራለን፡፡ ጠላቶቻችን ያጎደፉትን ስማችንን አስከብረን ሌሎች ህዝቦች ያገኙትን ጥቅም እኛም በእኩልነት ተጠቃሚ እንሆናለን፡፡
  2. ከሁሉም በላይ ደግሞ የሲዳማን ህዝብን ህልውና ለመናድ ለዘመናት ሲሰሩ የቆዩትን የፀረ- ሲዳማ ህዝብ ተኩላዎችን ዓላማ በማክሸፍ ዳግመኛ ላያገኙን ከእጃቸው ነፃ እንወጣለን፤ በባርነት ለመግዛት የሚሯሯጡትን፤ ለዘመናት ደማችንን ሲያፈሱ ከኖሩት ደኢህዴን ተኩላዎች ነፃ ወጥተን የፌደራል መንግስት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እናካሂዳለን፡፡ ያለ ደኢህዴን አማላጅነት፡፡
  3. ከሁሉም በላይ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት (Sdama National Regional State ) የሚል አዲስ ክልል በኢትዮጵያ ፖለቲካ እንመሰርታለን፡፡ አካባቢያችንና ከተማችንን ያለምንም ግርግርና ትንኮሳ በሰላም በራሳችን እናስተዳድራለን፡፡ ድንበራችንንና መሬታችንን ከመቸርቸር ተቆጥበን የድሮ ክብራችንን መልሰን በክብር እንኖራለን፤ ጤነኛ የሆነ ማህበረሰብ በንፁህ የሲዳማ ልጆች አዲሲቷን ሲዳማ እንገነባለን፡፡
  4. ያለንን እምቅ የተፈጥሮና የሰው ሰራሽ ሀብት በአግባቡ በመጠቀም( mobilization of immense resource ) በማድረግ ድህነት ከሲዳማ ብሎም ከሀገራችን ኢትዮጵያ እንዲጠፋ በማድረግ ዜጎች የሚያድጉበትን ሁኔታ እንፈጥራለን ክልልም ብንሆን፡፡ ደኢህደኖች ሆነ ብለው አቅደው ሀብታችን እንዲመናመን በማድረግ ድህነት እንዲስፋፋ ያደረጉትን መልሰን እራሳችንን በማልማት ሲዳማችንን የልማት መንደር እናደርጋታለን፡፡
  5. የራሳችን የሆነ የክልል በጀት ይኖረናል፡፡ ከፌደራል መንግስት የሚሰጠንን ድጎማ በማከል ልማታችንን እናፋጥናለን በምፅዋት መልክ የሚሰጠን ስጦታ ይቆማል፡፡ በራሳችን በጀት አካባቢያችንን እናለማለን
  6. የሲዳማ ልጅ በመሆናችን ብቻ ደኢህዴን የሚያደርስብ የእስራት መከራ ይቀራል፡፡ የሲዳማ ልጆች ሙሁራን ኮርተዉና ከበሮ .በእናት ሲዳማ ጉያ ላይ መኖር ይጀምራል፡፡ ጥቂት ሆዳሞች ሳይሆኑ ሙሁራንና ለህዝቡ የሚወግኑ የሲዳማ ልጆች ህዝባችንን ሲዳማን ወደ ፊት ይመሯታል፡፡
  7. በፌደራል ደረጃ በተለያዩ መንግስት መዋቅሮች ተመጣጣኝ የሆነ ዉክልና .በማግኘት የህዝባችንን ጥቅምና ክብር እንጠይቃለን፡፡ የሲዳማ የሆነው ሁሉ የሲዳማ ህዝብ ብቻ እንደሆነ ማሳወቅ፡፡
  8. የሲዳማ ክልል ሬዲዮና ቴሌብቪን ድርጅት በማቋቋም በራሳችን ቋንቋ በመጠቀም ህዝባችንን እናስተምራለን፡፡ ባህልና ወጋችንን እንዲሁም ማንነታችንን ፤የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ መሲቦቻችንን ላገር ውስጥና ለአለማ አቀፉ ማህበረሰብ እናሳያለን፡፡ ህዝባችን በባህሉ እንዲኮራ በማድረግ ትክክለኛውን ወቅታዊ መረጃ በቋንቋዉ እናስተላልፋለን፡፡ የሲዳማ ቋንቋ የሚዲያ(media) ቋንቋ ይሆናል፡፡ የሲዳምኛ ዘፈን በሚዲያ (media) መስማት ብርቅ እንደሆነብን አይኖርም ከደኢህደኖች የውሸት ሚዲያና ከስድባቸውም ነፃ እንወጣለን፡፡
  9. የራሳችን የሆነ ማንነታችንን የትግል ታሪካችንን የተፈጥሮ ሀብታችንን የሚያሳይ ሰንደ ቃለማ እናገኛለን(ይኖረናል)፡፡ የሲዳማ ክልል ሰንደ ቃለማ ብሩህ ተስፋችንን የሚያሳይ ይሆናል!!!
  10. የራሳችን የሆነ የክልል ምክር ቤት ህግ አውጪ ህግ፤ አስፈፃሚና የህግ ተርጓሚ አካል ይኖራል፡፡
  11. ህጎች በራሳችን ቋንቋ ይወጣሉ፤ ህዝባች በራሱ ቋንቋ ይዳኛል፤ ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ሰበር ነሰሚ ችሎት በሲዳምኛ ይዳኛሉ፡፡
  12. በመኪኖቻችን ላይ የሲዳማ ህዝብ የሚል ታርጋ ለጥፈን በማንነታችን የምናፍር ሳይሆን የምንኮራበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ጠላታችን ደኢህደን ያጨለመብን ተስፋችን እንደገና ፈንጥቆ ተከባብረን በእኩልነትና በነፃነት የምንኖርበት ክልል እንሆናለን፡፡
  • በምዕራብ አውሮፓና የቀድሞው ሶቬት ህብረት ….. ሲበታተን ነፃነታቸውን ያወጁት ሀገሮች በቆዳ ስፋትና በህዝብ ብዛት የሲዳማ ህዝብ በብዙ እጥፍ የማያንሱ ናቸው፡፡ እኛ ክልል መሆን አንችልም ከሚሉን የሟርተኞች ቀልድ አልፈን ሀገር መሆን የምንችል ህዝብ ነን፡፡
ይህ ደግሞ እውን መሆን የሚችለው እያንዳንዱ ተወላጅና ዜጋ የሚጠበቅበትን የዜግነት ግዴታ ሊወጣ ይገባል፡፡ ከላይ በዝርዝር የተገፁ እውነታዎች በምኞትና በህልም የሚሳኩ ሳይሆን በብርቱ ትግልና በቁርጠኝነት ራስን መስዋዕት በማድረግ ጭምር ነው፡፡ የጥንት የሲዳማ ዔጄቶዎች እነ አሊቶ ሄዋኖ ‘አይኔን አልጨፍንም ለመጪው ትውልድ እንዳጨልም ብለው ለእኛ ብርሃን አስረክበዋል፡፡ እነ ግራ አዝማች የተራ ቦሌ ሲገደሉ ‘ወደ ማዕከላዊ ሲዳማ ሀገር ሸሽቼ ከሞትኩ ለሲዳማ መሬት ይጠባል ’ በማለት ሩቅ ቦታ ተይዘው በመሄድ የሞት ፅዋ በመቅመስ ታላቋን የበረታች የዛሬይቱን ሲዳማ አስረክበዉናል፡፡
ውድ የትግል ጓደኞቻችን፤ ይህንን እውነታ ልብ በማለት በማስተዋል እስከመጨረሻው በመታገል የህዝብ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ መረባረብ ይኖርባችኃል፡፡ በሚቀጥለዉ እትማችን የሲዳማ ህዝብ ጠላት የሆነዉ ደኢሀወዴን የክልል ጥያቄያችንን ለማክሸፍ እያደረገ ስለሚገኘዉ መሰሪ ተግባር እንመለከታለን፡፡ ቸር እንሰንብት፡፡
ድልና ድምቀት ለተሰው ሰማዕታትና ለሰፊዉ ሲዳማ ህዝብ!!


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር