በቅርቡ ከእስር ቤት ወደ ሆስፒታል ስወሰዱ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የመኪና ግጭት ኣደጋ ደርሶባቸው የነበሩት ካላ ዱካሌ ላሚሶ
በኣደጋ ምክንያት በግንባራቸው ላይ የደረሰባቸውን ጉዳት ፎቶውን ኣጉልተው ይመልከቱ |
የ55
ዓመት እድሜ
ባለበት የሆኑት እና በአሁኑ ወቅት በማረሚያ
ቤት ሆነው በስኳርና የደም
ግፊት እየተሰቃዩ የሚገኙት ካላ
ዱካሌ ላሚሶ፣ በነሐሴ 10/2004
ዓ.ም
ከስራ ቦታቸው ታፍነው እስር ቤት የተወረወሩት፣
እስከዛሬ መስከረም 15/2005
ዓ.ም
ድረስ ክስ ሳይመሰረትባቸው በማረሚያ ቤት
የሚገኙት እና ለሲዳማ ሕዝብ መብት ሕይወታቸውን
ሙሉ ሲታገሉ የኖሩ፣በግብርና ዘርፍ ማስተርሳቸውን
በእንግሊዝ ሀገር በ1980ዎቹ
ያገኙት አቶ ዱካሌ ላሚሶ መስከረም 14/2005
ዓ.ም
ከጠዋቱ 4 ሰዓት
ላይ በቴክኒክና ሞያ ት/ቤት
አካባቢ ከወህኒ ቤት በፖሊስ ታጅበው ለደም
ግፊት ህክምና ወደ ሃዋሳ ሬፈራል ሆስፒታል
ሄደው ሲመለሱ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች
ከተጫኑበት ባጃጅ ጭምር ታርጋ በሌለው መኪና
ተገጭተው 4 ሜትር
በሚረዝመው የአስፋልት ጠርዝ ገደል ውስጥ
ጥለዋቸው ለጊዜው ተሰውረዋል፡፡በዚህም
አደጋው በደረሰበት አካባቢ ህብረተሰብ ርብርብ
ሕይወታቸው የተረፈ ሲሆን ታርጋ የሌለው
ተሸከርካሪም ለጊዜው ተሰውሯል፡፡
Comments
Post a Comment