በቅርቡ ከእስር የተፈቱት ታዋቂው የሲዳማ መብት ተከራካሪ ካላ ዱካሌ ላሚሶ ፍርድቤት እንድቀርቡ ቀጠሮ ተሰጣቸው፤ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ ኣስራ ሁለት የሹመት መደቦች ሲዳማ ባልሆኑ ግለሰቦች እንዲያዙ ተደረጉ

የሲዳማ መብት ተከራካሪ ካላ ዱካሌ ላሚሶ

ከሲዳማ የፊቼ በኣልን ተከትሎ በክልሉ መንግስት መሪነት ከታሰሩት በርካታ የሲዳማ ተወላጆች መካከል የሆኑት እና ከቅርብ ቀናት በፊት የእስር ቤት የተፈቱት ካላ ዱካሌ ሰሞኑን ወደ ፍርድቤት እንድቀርቡ የቀጠሮ ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።

ስማቸው እንድገለጽ ያልፈለጉ የውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናሩት ካለ ዱካሌ ላሚሶ የዩኒቨሪሲቲ ተማሪዎችን በመንግስት ላይ በማነሳሳት፤ ጸረ ኢህኣዴግ/ ደኢህዴን ጽሁፎችን በመጻፍ እና በመሳሰሉት ክስ እንደተመረሰረተባቸዋል።
እንደእነዚሁ የውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ገለጻ ከሆነ፤ የደቡብ ክልል ፕሬዚዴንት ካላ ሽፈራው ሽጉጤ የሲዳማን የክልል ጥያቄ ለመጨፍለቅ በምያደርጉት ጥረት በርካታ የሲዳማ ምሁራንን በማሰር ብሎም በማስፈራራት እያሸማቀቁ የቆዩ ሲሆን፤ ሰሞኑን ከፌደራል እስከ ወረዳ ያሉት የሲዳማ ኣመራሮችን በማሰባሰብ ደኢህዴን ለኣመታት ያልም የነበረውን የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማ ተወላጆች እጅ የመንጠቅ ህልማቸውን ኣሳክቷል።

የሲዳማ ኣመራሮች ያሳለፉትን ውሳኔ ተከትሎ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ ኣስራ ሁለት የሹመት መደቦች ሲዳማ ባልሆኑ ግለሰቦች እንዲያዙ ተደርገዋል።

የሲዳማን የክልል ጥያቄ የምደግፉት ሆነ የሃዋሳን ከተማ ከሲዳማ እጅ መውጣቱን የምቃወሙትን የሲዳማ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው የቃላት ዛቻ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፤ ካላ ዱካሌ ፍርድቤት እንድቀርቡ ልደረጉ ያሉት ውስጥ ውስጡን በመቀጣጠል ላይ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቀልበስ ታስቦ መሆኑን እነዚሁ ውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ኣብራርተዋል።


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር