የሲዳማ ዞን ከተማ ልማት መምሪያ በተያዘው የበጀት ዓመት በተለያዩ ከተሞች ከ8ዐ ኪሎ ሜትር በላይ አዲስ የጠጠር መንገድ ግንባታ ከ14 ኪሎ ሜትር በላይ ደግሞ የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ሥራ ለማከናወን ማቀዱን አስታወቀ፡፡


በሁሉም ማዘጋጃ ቤቶች አማካይነት 9ዐ ኪሎ ሜትር አዲስ የመንግድ ከፈታና ጠረጋ እንዲሁም 92 ኪሎ ሜትር የመንገድ መብራት 74 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የውሃ መስመር ዝርጋታ ከሚከናወኑ ተግባራት ተጠቃሽ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡
መምሪያው በዞኑ ከሚገኙ 42 ማዘጋጃ ቤቶች ሥራ አስኪያጆችና የስራ ሂደት አስተባባሪዎች ጋር በ2ዐዐ4 በጀት አፈፃፀምና በ2ዐዐ5 እቅድ ዙሪያ በተወያየበት ወቅት የመምሪያው ኃላፊ አቶ ለገሠ ማሬሮ እንዳሉት በተያዘው የበጀት ዓመት ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ የሚያደርጉ፣ ለወጣቱ ደግሞ የሥራ እድል የሚያስገኙ ሥራዎች በተጠናከረ መልኩ ይከናወናሉ፡፡

በዚህም መሠረት 9ዐ ወጪ ቆጣቢ እና ተጀምረው ያልተጠናቀቁ 33ዐ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንዲሁም በ482 ነባር የመንግስት ቤቶች ላይ የጥገና ሥራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል፡፡
ውይይቱን በንግግር የከፈቱት በዞኑ ዴህኢህዴን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የከተማ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በየነ በራስ በበኩላቸው ማዘጋጃ ቤቶች ለኢንድስትሪ መስፋፋት መሠረት በመሆናቸው ለከተሞች እድገት ዋንኛ እንቅፋት የሆነውን የኪራይ ሰብሳቢነት ሰንሰለትን መበጣጠስ አለብን ብለዋል፡፡ የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/30MesTextN1005.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር