በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ የኑራ ቆራቴ አገልግሎት ህብረት ሥራ ማህበር በ7 ቀበሌያት ለሚገኙ 11 አንደኛ ደረጃ 1ኛና 2ኛ...፡፡


በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ የኑራ ቆራቴ አገልግሎት ህብረት ሥራ ማህበር በ7 ቀበሌያት ለሚገኙ 11 አንደኛ ደረጃ  1ኛና 2ኛ ሳይክል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከ1ዐዐ ሺህ ብር በላይ ወጪ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
የትምህርት ቁሳቁስ ተገዝቶ የተሰጣቸው ወላጆቻቻው የማህበሩ አባላት ለሆኑ ተማሪዎች ነው ተብሏል፡፡
የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ማቴዎስ ዲጋሳ በዚህን ወቅት እንዳሉት ተገዝቶ በተበረከተው የትምሀርት ቁሳቁስ 4 ሺህ 554 ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ በርካታ ተማሪዎች የትራንስፖርትና የትምህርት ወጪ መሸፈኑንም ገልፀዋል፡፡
የወረዳው ግበይትና ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘማች እርጥባ በበኩላቸው ማህበሩ እያደረገ የሚገኘው በጎ ተግባር አርሶ አደሩ የማህበሩ አባል በመሆኑ ብቻ ከራሱ አልፎ ቤተሰቡም ጭምር ተጠቃሚ መሆኑን ማረጋገጫ እንደሚሆን አመልክተዋል፡፡
ሌሎች ማህበራትም ይህን አርያ እንዲከተሉ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳይ ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/26MesTextN205.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር