4ተኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና 3ተኛ የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ከነገ በስቲያ ይጀምራል


አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2005/ዋኢማ/ - አራተኛው የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የ3ኛው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የስራ ዘመን ከነገ በስቲያ የጋራ የመክፈቻ ስብሰባቸውን  እንደሚጀምር ተገለፀ።

የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስብሰባ ከነገ በስቲያ ከቀኑ 8 ሰዓት የሚጀምር ሲሆን፤ በስብሰባው ላይ የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ የመክፈቻ ንግግር ያደርጋሉ።

የመክፈቻ ስነ-ስርዓቱን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ የሚያስተላልፍ ሲሆን፤ መስማት ለተሳናቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም የምልክት ቋንቋ በቀጥታ ለህዝቡ እንደሚሰራጭ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር