በሲዳማ ዞን የአሮሬሳ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሠራተኞች ለህዳሴው ግድብ ለ2ኛ ጊዜ በ1 ወር ደመወዛቸው ቦንድ ለመግዛት መስማማታቸውን ገለጹ፡

የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ማሞ እንዳሉት ሠራተኞቹ ለቦንድ ግዥው ደመወዛቸውን የሚቆርጡት ከጥቅምት ወር ጀምሮ ነው፡፡

የወረዳው ደኢህዴን ን/ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጋቢሶ ጋቢባ በበኩላቸው በትምህርት ጥራት ላይ ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት ህዝቡ፣ መንግሥትና ድርጅት የአንድ ዓላማ የልማት ሠራዊት ሆነው መሥራት አንዳለባቸው አመልክተዋል፡፡

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ዎራና ትምህርት ቤቶችን ቁጥር 53 በማድረስ በትምህርት ተደራሽነት ላይ የተገኘውን ስኬት በትምህርት ጥራትም ላይ መድገም አለብን ብለዋል፡፡ ዘገባው የሲዳማ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን  መምሪያ ነው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር