1433ኛው የዒድ አል አድሃ አረፋ በዓል ዛሬ እየተከበረ ነው



አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) 1ሺህ 433 ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው ።

ከስያሜው ጀምሮ ከነቢያት አባት ከኢብራሂም አሌሂሰላም ታሪክ ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ ያለው የአረፋ በዓል ፥ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ የእርሳቸውን ታሪክ በማስታወስ ለሰው ልጅ ደህንነት የከፈሉትን መስዋዕትነት በየዓመቱ የሚዘክሩበት በዓል ነው ።

በቅዱስ ቁርአን እንደመለከተው ነብዩ ኢብራሂም ልጃቸው እስማኤልን በአላህ ትእዛዝ ለመስዋት ሲያዘጋጁ ፤ በምትኩ ሙክት በግ መስዋት መቅረቡን ያሳያል በዚህም ኢድ አል አድሃ የመስዋት በዓል ተብሎ ይከበራል።

በዓሉ ኢድ አልአድሃ ተብሎ የሚከበረውም ኡዲሂያ ወይም መስዋዕት ስለሚታረድ መሆኑን ፥ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ አህመዲን ሼህ አብዱላሂ ጨሎ ይናገራሉ።

በዚህ ታላቅ ሃይማኖታዊ ቀን እርስ በርስ መዘያየርና ደስታን መገላለጽ በፈጣሪ ዘንድ በእጅጉ የሚወደድ ተግባር ነውና ከሁሉም ይህ ይጠበቃል።

በአሉ ሲከበርም ሁሉም የእምነቱ ተከታይ በዓሉን በደስታ ያከብር ዘንድ ያለው ለሌለው መዘየር ዋነኛ ተግባር ይሆናል።

በኢድ ቀን ከሚፈጸሙት ኢባዳዎች አንዱ ኡዲሂያ ሲሆን ፥ ለኡሂዲያ ከሚታረደው ከብት መካከል ለጎረቤትና ለተቸገሩ ማጋራት የእምነቱ ስርዓት ያዛል።

የበአሉ አካል የሆነው የስግደት ስነ ስርዓት /ሶላት/ ማለዳ 1 ሰዓት ከ30 ላይ በጋራ በየአካባቢው እየተካሄደ  ሲሆን ፥ በመዲናችን አዲስ አበባም የሶላት ስነ ስርዓቱ በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተፈጸመ ይገኛል ። 
የበአሉ አካል የሆነው የስግደት ስነስርዓት /ሶላት/ ማለዳ ላይ በጋራ በየአካባቢው የተካሄደ  ሲሆን ፥በመዲናችን አዲስ አበባም የሶላት ስነስርዓቱ በአዲስ አበባ ስታዲየም በሺዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ተከብሯል ።  

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር