የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ13 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ወጪ በከተማው ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ክፍት የሆኑ የጐርፍ መውረጃ ቦዮችን በኘሪካስት ለመሸፈን የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡


የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት  በ13 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ወጪ  በከተማው ውስጥ  በተለያዩ አካባቢዎች ክፍት የሆኑ የጐርፍ መውረጃ ቦዮችን በኘሪካስት ለመሸፈን የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡
ለማህበራት ፣ ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት እንዲሁም ለተለያዩ ተቋማት  ግንባታ ለጨረታ የሚቀርብ ከ4ዐዐ ሄክታር በላይ መሬት መዘጋጀቱንም አመልክቷል፡፡
ማዘጋጃ ቤቱ በ2ዐዐ4 አፈፃፀምና በ2ዐዐ5 የሥራ እቅድ ላይ የጋራ ውይይት አካሂዷል፡፡
የሀዋሣ ከተማ ውብ እና ፅዱ ሆና ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻነቷን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የከተማው አስተዳደር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በተለይም በማዘጋጃ ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተጀመረው መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ማጠናከር አንዱ ነው፡፡
ማዘጋጃ ቤቱ በ2ዐዐ4 የሥራ ዘመን በከተማ ኘላን ዝግጅት፣ በመሬት አስተዳደር፣ በየክፍለ ከተማው የተገኙትን ሠነድ አልባ ፋይሎችን በካዲስተር በማደራጀት ፣ በመሠረተ ልማት  አቅርቦት እንዲሁም በፅዳትና ውበት፣ መናፈሻ አገልግሎት በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡
የከተማው ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩ ወልዴ እንደገለፁት በከተማው ከ2 ዓመት በላይ ሳይለሙ የቆዩ 7 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት በከተማው አስተዳደር ውሳኔ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ተወስኖል፡፡

ከ27 ኪሎ ሜትር በላይ አዲስ የጐርፍ መውረጃ ቦይ ቁፋሮ ስራና  19 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር ነባር ቦይ መገንባቱንም አመልክተዋል፡፡
በከተማው ውበት ፣ ልማትና መናፈሻ አገልግሎት ዘመቻ ከ48 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በድንጋይ ንጣፍ ሥራ በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ ከ5 ሺህ 2ዐዐ በላይ ዜጐች የሥራ እድል ተፈጥሮል፡፡
በቀበሌና ቁጠባ ቤቶች እየኖሩ የራሳቸውን መኖሪያ ቤት ከሠሩ በኃላ ሳያስረክቡ በደባልነት የሚጠቀሙ ግለሰቦችን የመለየት ሥራ በተያዘው እቅድ ዘመን በትኩረት እንደሚሠራም ነው  ሥራ አኪያጁ የገለፁት፡፡
አንዳንድ የጉባኤ ተሳታፊዋች በበኩላቸው በየከፍለ ከተሞቹ የራሳቸው መኖሪያ ቤት እያላቸው የመንግስትን ቤት ስለሚጠቀሙ ግለሰቦች ፣ ክፍት የተተወ ቦዮች  የሚያደርሱትን ጉዳትና በውስጥ ለውስጥ መንገድ ላይ ተበላሽተው አገልግሎት መስጠት ያቆረጡ የመብራት ፍሎረንሰቶች መስተካከል እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡
በተለይም በምሥራቅ ፣ በታቦር፣ በሀይቅ ዳር እና መሀል ክፍለ ከተማ ክፍት የሆኑ የጐርፍ መውረጃ ቦዮችን በኘሪካስት ለመሸፈን በ2ዐዐ4 መገባደጃ በ13 ነጥብ 7 ሚሊዮን የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የማዘጋጃ ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩ አስረድተወል፡፡
ተበላሽቶ የነበረው የመብራት አገልግሎትም እድሳት እንደሚደረግበት ጠቁመዋል፡፡
በ2ዐዐ5 ፍትሀዊ የመሬት አቅርቦትን በማሳደግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በማህበራትና በግል ቤት ሠሪዎች ለሚገነቡ ግንባታዎች፣ ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት እንዲሁም ለተለያዩ ተቋማት ግንባታ 4ዐ4 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱንም ጠቁመዋል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/25MesTextN305.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር