ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል በተያዘው ዓመት ከ116 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በቡና ይለማል


አዋሳ ጥቅምት 08/2005 በደብብ ክልል በተያዘው የምርት ዘመን ከ116 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በቡና እንደሚለማ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። ለተከላው ከ320 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ይዘጋጃል። 
በክልሉ ግብርና ቢሮ የመንግስት ኮሚኒኬሽን የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ አያሌው ዘነበ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በክልሉ ቡና አብቃይ በሆኑ ወራዳዎች 116 ሺህ 648 ሄክታር መሬት በስግሰጋና በአዲስ በቡና ይለማል።
በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በክልሉ ቡናን በብዛትና በጥራት በማምረት የሚገኘውን የውጪ ምንዛሪ መጠን ለማሳደግ ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። 
በምርት ዘመኑ በክልሉ በቡና የተሸፈነውን መሬት መጠን 22 በመቶ ለማሳደግ በተያዘው ግብ መሰረት ምርጥ የቡና ዘር በማሰባሰብ በግብርና ምርምር ማዕከላት፣ በመንግስት፣ በባለሀብትና በአርሶ አደሩ የችግኝ ጣቢያ ከ122 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ምርጥ የቡና ዘር በማፍሰስ የችግኝ ዝግጅት እንደሚደረግ አስታውቀዋል። 
በቡና ተከላ ስራ ለሚሰማሩ ከ438 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች በቡና ማሳ ዝግጅት ተከላ እንክብካቤ አሰባሰብና አከመቻቸት ዙሪያ በተግባር የታገዘ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑንም አቶ አያሌው ገልጸዋል። 
በክልሉ በቡና ከለማውና ለምርት ከደረሰው 349 ሺህ948 ሄክታር ማሳ ከ3 ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱንና የቡና ምርታማነትን በሄክታር 10 ነጥብ 5 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። 
ዘንድሮ በቡና ለሚሸፈነው ከ116 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት 320 ሚሊዮን 895 ሺህ 915 የቡና ችግኝ ዝግጅት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ አቶ አያሌው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ገልጸዋል።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=2791&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር