ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እና ሲዳማ


ፉቄ ዲሬሞ ከሃዋሳ
የሲዳማ የራስ ገዝ የክልል ኣስተዳደርን በተመለከተ በህዝቡ ዘንድ የምነሱት ጥያቄዎች እድሜ ጠገብ ናቸው። ኣብዛኛዎች እንደምገምቱት በተለይ ከዛሬ ኣስር ኣመት ወዲህ የተጀመረና ከግዜ ወደ ጊዜ በህዝቡ ዘንድ እየሰረጸ የመጣ ጉዳይ ሳይሆን የሲዳማ ህዝብ ላለፉት ከሰላሳ ኣመታት በላይ ለነጻ ዲሞክራሲያዊ የራስ ኣስተዳደር ሲያደርግ ነበረው ትግል ኣካል ነው።

የሲዳማ ህዝብ ከማንም የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ቀደሞ ለራስ ገዝ ኣስተዳደር እና ለመልካም ኣስተዳደር ብሎም ለዲሞክራሲያዊ ስርኣት መስፈን የታገለ ህዝብ ነው። ይህም ማለት የሲዳማ ህዝብ መልካም ኣስተዳደር እና የዲሞክራሲያዊ ስርኣት ግንባታ ኣስፈላግነትን በቅጡ የተረዳ ብሎም ሲታገልለት ቆየው ህዝብ ነ፤ ለስኬቱም ብሆን ኣያሌ ውድ የሲዳማ ልጆች መስዋዕት ሆኖለታል እየሆኑም ይገኛል።

የሲዳማ የምንም ጊዜ ውድ ልጆቿ የተሰውለት የመልካም ኣስተዳደር እና ዲሞክራሲያዊ የክልል ኣስተዳደር በተለይ ከሃያ ኣመታት በፊት በሲዳማ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላዋ ኢትዮጵያ የነበረው የደርግ ስርኣት ተገርስሰው ኣዲስ ስርኣት ሲቋቋም እውን ሆኖ ነበር ብሆንም ከጥቂት ጊዚያት በኃላ የራስ ክልል ኣስተዳደር መብቱን እንደገና መነጠቁ ይታወሳል።

የሲዳማ ህዝብ ከመቶ ኣመታት በላይ ከሌሎች የኣገሪቱ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር ተፋቅሮ፤ ተቻችሎ በኣንድነት የኖረ ህዝብ ብሆንም ፖለቲካዊ የራስ ገዝ ክልላዊ ኣስተዳደሩን መነጠቁ እና ከሌሎች ኣናሳ ብሄሮች ጋር በስሜ ደቡብ በኣንድ ክልል ውስጥ መጠፈሩን ሳይቀበለው ኖሯል።

በኢህኣዴግ የምመራው መንግስት የወሰደውን ይህንን እርምጃ በተመለከተ በወቅቱ ህዝቡ ተቃውሞውን በተለያዩ ኣጋጣሚዎች እና በተለያየ መልኩ የገለጸ ቢሆንም ሰሚ ሳያገኝ ቀርቷል። ከዚህም ባሻገር በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሱ ልጆች መተዳደሩ፤ በራሱ ቋንቋ የመማሪ እና የመዳኘት መብት ባለቤት መሆኑ ብሎም ኣዲስ በተመሰረተው የደቡብ ኢትዮ ጵያ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ ኣስተዳደር በኣስተዳደራዊ እርኬኖች ውስጥ የኣንበሳውን እጅ ማግኘቱ በወቅቱ ውስጥ ውስጡን ይቀጣጠል የነበረውን የራስ ክልል ኣስተዳደር ጥያቄ ልያስክነው ችሏል።

ነገር ግን ከግዜ ባኃላ የሲዳማ ህዝብ የራሱን ክልላዊ ኣስተዳደር መብት ኣጥቶ ከሌሎች ጋር መጠቃለሉ የኣገሪቱ ህገ መንግስት በምፈቅደው መሰረት ማግኘት ይገባው የነበራቸውን ኣያሌ መብቶቹን እንዲያጣና የሚያገኛቸውን እድሎች ብሆን ከሌላው ጋር እንዲጋር የግድ መሆኑ እና ከሌሎች ካጋጠሙት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች መጓደል ጋር ተያይዞ ለጥቅት ጊዚያትም ብሆን ስክኖ የነበረውን የራስ ክልል ጥያቄ ኣቀጣጥሎታል።

ራስን በክልል ደረጃ የማስተዳደር ጥያቄን እንደየመጨረሻ ኣማራጭ በማስቀመጥ ሌሎች የመልካምኣስተዳደር ጥያቄዎችን ያነሳው የሲዳማ ህዝብ በመልካም ኣስተዳደር ችግሮቹ ላይ ያነሳቸውን ጥያቄዎች በተለያዩ ጊዚያት እና በተለያዩ መንገዶች በወቅቱ የኣገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለነበሩት ለኣቶ መለስ ዜናዊን ጨምሮ በየደረጃ ላሉ ጉዳዩ ለምመለከታቸው መንግስታዊ ኣካላት ያቀረበ ቢሆንም በእነዚሁ መንግስታዊ ኣካላት ባለስላጣናትን ልክ እንደየማዳ ጫዋች ከቦታ ወደ ቦታ በመቀያየር የተሰጡ ምላሾች ኣጥጋቢ ኣልነበረም።

ኣነሰም በዛም ለሲዳማ ህዝብ የልማት ጭላጭል ያሳይ የነበረውን የኣቶ ኣባቴ ኪሾን ኣስተዳደር በሙሲና እና በሌሎች ጉዳዮች ሰበብ ኣስባብ ከስልጣን ላይ በማንሳት የክልሉን ርዕሰ መስተዳደሪነትን የተረከበው የኣሁኑ የኣገርቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በኣቶ ኃይለማሪያ ደሳለኝ ይመራ የነበረው የክልል ኣስተዳደር በሲዳማ ዞን ውስጥ ይከተለው በነበረው የተበላሽ የመልካም ኣስተዳደር እና ሰብኣዊ መብት ጥሰት ከህዝቡ የፍትህ እጦት ብሎም የልማት መጓደል ጋር ተያይዞ እንኳል ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ እንድሉ ሆነና ህዝቡን ለኣደባባይ ኣበቃው፤ የዛሬ ኣስር ኣመት በሎቄ ጉድማሌ ተሰብሰቦ በመፍትሄዎቹ ላይ እንዲመክር ኣስገደደው።

በብዙ ሺዎች የምቀጠር ህዝብ ለቀናት የመከሩት የሲዳማ ሽማግሌዎች በሰጡት ውሳኔ መሰረት ጥያቄውን ለምመለከተው መንግስታዊ ኣካለት በሰላማዊ ስልፍ ለመቅረብ የወጣ ሲሆን የወጣው ህዝብ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በተከፈተባቸው የገዳይ ጥይት እሩምታ በመቶዎች የሚቆጠሩት ለሁለተኛ ጊዜ ለሲዳማ ህዝብ የራስ ክልል ኣስተዳደር ተሰውተዋል።

ለመቶዎች የሲዳማ ተወላጆች መገደል ብሎም በወቅቱ ለነበረው የሰብኣዊ መብት ረገጣ ዋነኛ ኣንቀሳቃሽ ሞተር ከሆኑት ግለሰቦች መካከል የወቅቱ የደቡብ ክልል ፕረዚዳንት ብሎም በኣሁኑ ጊዜ የኣገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ኣንደኛው ግንባር ቀደሙ ሲሆኑ፤ መለሰ ማሪሞ፤ በረከት ስሞኦን፤ ኣባዱላ ገመዳ እና ሌሎች ባፈሰሱት የንጽሃን ሲዳማዎች ደም በኣሁኑ ጊዜ ለከፍተኛ መንግስታዊ ስልጣን የበቁ ይገኑበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ ኃይለማሪያ ደሳለኝ እና ሌሎች የወቅቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በእጃቸው የሲዳማዎች ደም ስላለባቸው ለፍርድ ቀርበው የሚገባቸውን ቅጣት ማግኘት እያለባቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ለተሻለ ስልጣን በመታጨት እና በመሾም ላይ ናቸው።

እነ ኣቶ ኃይለማሪያም በመቶዎች የሚቆጠሩትን ሲዳማዎች በጠራራ ጸሀይ በግፊ ካስገደሉ በኃላ የሲዳማ የራስ ገዝ የክልል ኣስተዳደር ጥያቄን ኣሳንሰው ከሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ጥያቄ ደረጃ በማውረድ ለህዝቡ ያላቸውን ንቀት ኣሳይተዋል። ያስገደሏቸውን ሲዳማዎች ጸረ ስላም በማለት ተሳልቀውባቸዋል። የንቀታቸው ንቀት ለሲዳማ ህዝብ የራስ ክልል ኣስተዳደር ምላሽ የሲዳማን ደም ከማፍሰሳቸው ባሻገር የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማዎች እጅ በመንጠቅ የኣገሪቱን ህገመንግስት ተጻረዋል።

ቀጥሎ ባሉት ኣመታትም በሲዳማ ዞን ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩት የልማት ድርጅቶችን በመበተን በዞኑ የነበረውን የልማት እንቅስቃሴ ኣስተጓጉለዋል የሲዳማን ኢኮኖሚያዊ ኣድቋል።

ይቀጥላል

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር