በቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባና ሌሎች የከተማዋ አስተዳደር ሃላፊዎች ላይ ፍርድ ቤት ትእዛዝ አስተላለፈ


አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2005  (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የቀድሞውን የሀዋሳ ከንቲባ ጨምሮ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ላይ በነበሩ የከተማዋ አስተዳደር ሃላፊዎች በተከሰሱበት በእነ አቶ እንድርያስ ኦሌሳ መዝገብ የተለያዩ ትአዛዞችን አስተላለፈ፡፡

 ከመሬት ጋር በተያያዘ ያልተገባ ጥቅም ለራሳቸውና ለቤተሰቦቿቸው ለማስገኘት በማሰብ ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የተከሰሱት እነዚሁ የከተማዋ አስተዳደር የተለያዩ ሃላፊዎች የፍርድ ሂደት የሀዋሳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲመለከተው ቢቆይም በነጻ አሰናብቷቸው ነበር፡፡

የከልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩን ማየት ከጀመረ በኋላ ግን ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ያልቻሉትን 1ኛ ተከሳሽ እንድሪስ አሎሳና 2ኛ ተከሳሽ ጉደታ ጎምቢ በፖሊስ ተፈልገው ሊገኙ ስላልቻሉ ስማቸውና ምስላቸው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ እንዲፈለጉ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡

ፍርድ ቤቱ በዚሁ መዝገብ የተከሰሱ የሌሎች 4 ተከሳሾች የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ትእዛዝ ማስተላለፉን ነብዩ ይርጋአለም ዘግቧል።


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር