ቀይ መብራት --የሃይለማርያም ደሳለኝን እና የደመቀ መኮንን የተደበቀ ታሪክ

አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ደቡብ ክልል በነበሩበት ጊዜ የራሳቸውን የብሔረሰብ አካላት ወደ ስልጣን የመሰብሰብ ስራ ሲሰሩ ከሲዳማ ማህበረሰብ በኩል ለምን እኛስ ? የሚል ጥያቄ መነሳቱን የቅርብ ምንጮች ይጠቁማሉ ፤ አቶ ኃ/ማርያም ለዚሀ የሰጡት መልስ “ከእናንተ የተማረ ማህበረሰብ ስለሌለ ነው ካቢኔውን በተማረ ማህበረሰብ ያዋቀርኩት” የሚል መልስ ነበር



(አንድ አድርገን መስከረም 10 2005 ዓ/ም)፡- አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ እና የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ አቶ ደመቀ መኮንን የትምህርት ሚኒስትር ፤ አቶ ሶፊያን አህመድ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ፤ እነዚህ  በስም የተዘረዘሩት ሶስት ከፍተኛ የሀገሪቱ ቱባ ባለስልጣናት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በህይወት በተለዩበት ወቅት የኢህአዴግ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ለውድድር ያቀረባቸው ሰዎች ናቸው ፡፡ ፓርቲው ባደረገው ምርጫ መሰረት አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝን ሊቀመንበር ፤አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መሾሙ የሚታወቅ ነው ፤ በቂ ድምጽ ያላገኙት በወ/ሮ አዜብ መስፍን የተጠቆሙት አቶ ሶፍያን አህመድ በሶስተኝነት ወደ ኃላ ቀርተዋል ፤ ነገ 11/01/2005 ዓ.ም ፓርላማው ምርጫውን በ99.6 በመቶ ድምጽ ያጸድቀዋል ተብሎ ይጠበቃል ፤ አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የOnly Jesus እምነት ተከታይ ናቸው ፤ ምክትላቸው አቶ ደመቀ መኮንንና አቶ ሶፍያ አህመድ ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታይ ናቸው ፤ በመሰረቱ ደመቀ መኮንን ብሎ የእስልምና እምነት ተከታይ ይኖራል ብለው ሰዎች ላያስቡ ይችላሉ ፤  አቶ ደመቀም ከወደ ወሎ መሆናቸው ሰዎች ይናገራሉ ፤ አሁን እኛን ያሳሰበን ነገር የኢህአዴግ የፓርቲ ምርጫ አይደለም ፤ የነዚህ ሰዎች ሹመትም አይደለም ፡፡

የዛሬ 10 ዓመት ገደማ አቶ አሊ አብዶ በስልጣን በነበሩበት ጊዜ በጣም ቁልፍ የሆኑ አሁን ድረስ አከራካሪ የሆኑ ቦታዎችን በበታች ባለስልጣኖችና በእሳቸው ከለላ አማካኝነት በርካታ ቦታዎችን በሊዝና ከሊዝ ውጪ ሰጥተዋል ፤  አቶ አሊ አብዶ የአዲስ አበባ መስተዳድር በነበሩበት ጊዜ በቀጥተኛም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ከእሳቸው ትዕዛዝ በማውረድ በጥቂጥ ዓመታት ውስጥ 98 ያህል መስኪዶችን በአዲስ አበባ ማሰራት ችለው ነበር ፤ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙትን 132 አብያተክርስትያናት ለመስራት በ1826 ዓ.ም የታነጸው የቀራንዮ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ጀምሮ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ለመድረስ የ170 ዓመት ጊዜያትን ወስደዋል ፤ ባሳለፍነው ጥቂት ዓመታት ብቻ በአዲስ አበባ የመስኪዶች ቁጥር በ40 ልቀው ተገኝተዋል ፤ በአሁኑ ሰዓት በየአብያተክርስቲያናቱ በጥቂት መቶ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙት መስኪዶች የአቶ አሊ አብዶ ለቀጣይ ትውልድ ያስቀመጡላቸው ትሩፋቶቻቸው ናቸው ፤ ለገሀር ባቡር ጣቢያ ውስጥ ከባቡር ጣቢያው መሬት  በኪራይ በመውሰድ ህገ ወጥ መስኪድ የተሰራው የዚያን ጊዜ ሰሞን ነው ፤ በአዲስ አበባ በየዓመቱ የቦታ ኪራይ እየተከፈለበት የቆመ መስኪድ ቢኖር የለገሀሩ መስኪድ አንዱ ነው(ዓመታዊ ኪራይ የተከፈለበትን ሰነድ በእጃችን አለ) ፤ ወደፊት መንግስት መሬቱን እፈልገዋለሁ እና ልቀቁ ቢል እንኳን ሊነሳ የሚችለውን ችግር መገመት አያዳግትም ፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም በለገሀር ባቡር ጣቢያ ግቢ ውስጥ በህገወጥ የተያዙትን ቦታዎች በ”አይናችን” ፕሮግራም ላይ ሲያቀርብ የመስኪዱን ነገር ማንሳት ግን አልፈለገም  ፤ ይህ ጥያቄ ቢነሳ ቦታው በኪራይ ከባቡር ጣቢያው እንደተከራዩ የሚያውቁት ጥቂት ሰዎች በመሆናቸው ችግር ይፈጠራል የሚል ስጋት አለ ፤ ሙስሊሞች በመንግስትና በአማኙ መካከል ባሉት ሰዎች አማካኝነት ይህን የመስኪድ ጥያቄ መፍታት የሚችሉ ባለስልጣናት በየቦታው አሏቸው  ፤ ይህ ጉዳይ በጥቂት በመንግስት ስልጣን ላይ በተቀመጡ የእምነቱ ተከታዮች አማካኝነት በቀላሉ ሊከናወን ችሏል ፡፡
የኢትዮጵያ ታሪክ ከተነሳ ቀድማ ስሟ የሚነሳው የኢትዮጵየ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ናት ፤ ኢትዮጵያ ትልቁ ታሪኳ ቤተክርስትያናችን ላይ ያጋደለ ሆኖ ያገኙታል ፤ ከዘመናት በፊት በአማርኛ እና በግዕዝ ቋንቋዎች በብራና ላይ ተጽፈው የሚገኙ ተዓምረ ማርያም ፤ የአራቱ ወንጌላውያን መጽሀፍቶች ፤ ገድሎች እና ድርሳናት የሚገኙት በኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ውስጥ ነው ፤ ከነዚህ ዘመን ከማይሽራቸው መረጃዎች በተጨማሪ በርካታ ንዋየ ቅዱሳት በተለያዩ የሀገሪቱ ሙዝየም ውስጥ ይገኛሉ ፤ ነገር ግን ባለፉት 15 ዓመታት የእነዚህ የበላይ ጠባቂ ሚኒስትር ማነው ? ብለው ቢጠይቁ መልሱን የተገላቢጦሽ ሆነው ያገኙታል ፤ ይህን የቤተክርስትያኒቱን ቅርስ የያዘ ተቋም መንግስት ባለፉት 10 ዓመታት አስተዳዳሪ አድርጎ የሾመው አቶ መሀመድ ድሪልን ነበር ፤  አቶ መሀመድ ድሪል ለ10 ዓመት ያስተዳደሩትን ሚኒስትር መስሪያ ቤት እሳቸው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የግብጽ አምባሳደር ተደርገው በተሾሙበት ወቅት በእሳቸው ቀጥታ ጠቋሚነት ቀጥሎ የተሾመው ሰው የእስልምና እምነት ተከታይ ነው ፡፡ እንዴት ነው ነገሩ ? የሚያስብ ጉዳይ መሆኑን ብዙዎች ሲናገሩ ይሰማል፡፡ የዛሬ ዓመት ገደማ ሙስሊም ማህበረሰብ በሚሊኒየም አዳራሽ ትልቅ አውደ ርዕይ አዘጋጅተው ነበር ፤ በጊዜው ከመቶ ክፍለ ዘመኖች በፊት ተጻፈ የተባለ ብራና ተመልክተን እጅጉን ገረመን ፤ የገረመን ነገር በአዲስ ብራና 50 ዓመት እንዳስቆጠረ እንኳን በCarbon dating ያልተረጋገጠን ቁርዓን ከዘመናት በፊት ተብሎ መቅረቡ ነው ፤ ይህ ቁልፍ ቦታ ላይ የተቀመጡት ሰዎች አስተዋጽኦ ይኖርበት ይሆን? ብለን እንድናስብ አስገደደን  (እንዲህ አይነት ነገሮችን ወደፊት…እንመለስበታለን)
የዛሬ 2 ዓመት ገደማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የባህልና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሃላፊ የነበሩት የእስልምና እምነት ተከታይ ነበሩ ፤ የዛሬ ሶስት ወር ግድም በቴሌቪዥን የተመለከትናቸው የባህልና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሃላፊ ደግሞ ሌላ በቀድሞ ሃላፊ የተተኩ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ሰውን ነው ፤ በመንግስት መሾሙ ብቻ ሳይሆን ቀጣይ ዱላ ተቀባይን አሳቢ ያደረገ ስራ እንደሆነ ያመላክታል ፤ በዚህ አይነት ውስጥ ለውስጥ ያለው ትስስር የጠበቀ ከመሆኑ የተነሳ ወደፊት የሚመጡትና በዚህ ቦታ ላይ የሚቀመጡ ሰዎች እምነታቸው ከዚህ ይወጣል የሚል እምነት የለንም ፤ ለዚህ ቦታ የሚመጥኑ በርካቶች እያሉ ለ15 ዓመታት የተለያዩ የስልጣን ተዋረድ ላይ ያሉን ሰዎች በአንድ እምነት የበላይነት ማስቀጠሉ ወደፊት ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ መስሎ ይታየናል፡፡
መሪ ስትራቴጂ
በእስልምና እምነት ውስጥ ያሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ከበታች ያሉት ከፍተኛ ሃላፊዎች በተቻላቸው መጠን የመንግስትን ህግ ሳያፋልሱ እምነታቸው ሲያድሩ ተስተውሏል ፤ ከ4 ወር በፊት በፍርድ ቤት አካባቢ የሚገኙ 13 መንግስት የሾማቸው ዳኞችና አቃቢ ህጎች በጠቅላይ ፍርድ ቤት አንድ ቢሮ ውስጥ በእለተ ቅዳሜ ከስራ ሰዓት ውጪ ተሰብስበው ወቅታዊ ጉዳያቸውን መነጋገራቸው ፤ የወደፊት አካሄድ ማስቀመጣቸው ተደርሶበት ከመንግስት ቀጭን ትዕዛዝ መተላለፉን ገልጸን መጻፋችን ይታወቃል ፤ ይህ የመንግስትን እና የህዝብን ሃላፊነት ወደ ኋላ በማለት የሚደረግ ሴራ በአንድም ይሁን በሌሎች ቦታዎች ሲከናወን ማየትና አቤቱታ መስማት እየተለመደ መጥቷል ፤ ይህ ነገር ሀገሪቱን ወዴት እንደሚወስዳት አመላካች መስሎ ይታየናል ፤ በአሁኑ ሰዓት የእስልምና እና ሌሎች የእምነት ተከታዮች ያስቀመጡት ስትራቴጂ ቢኖር የመተካካት መንገድ አንዱ ነው ፤ ነገሩ  ኢህአዴግ እንደሚለው ዱላ ቅብብል መሆኑ የገባቸው ይመስላሉ ፤  እነዚህ ሰዎች በስልጣን ላይ ሳሉ በርካቶችን በእምነት የሚመስሏቸውን የማስጠጋት ስራ ሲሰሩ ይታያሉ ፤ ቀድሞ የነበረው ኃላፊ ሲነሳ በአካባቢያቸው የሰበሰቧቸውን ሰዎች ለኃላፊነት በማጨት እንዲሾሙ ያደርጋሉ ፤ የእነዚህ ሰዎች የእርስ በርስ ቁርኝት ከሚታሰበው በላይ መሆኑን የተመለከተ ሰው  አንዳች ጥርጣሬ ውስጡ መጫሩ አይቀሬ ነው፡፡
በሀረር ውስጥ የሚገኝውን ጀጎል ግምብ በማለት የሚጠራው በድንጋይ የታጠረ አካባቢ በእስልምና ከካ ቀጥሎ ሁለተኛ ቅዱስ ቦታ ለማድረግ ውስጥ ውስጡን ስራ እየሰሩ መሆኑን ነገሩን የሚያውቁ ከውስጥ ሰዎች መረጃው ደርሶናል ፤ ከሁለት ዓመት በፊት የተጀመረው ይህ ስራ በውስጡ የሚገኙትን የክርስትና እምነት ተከታዮች ከፍተኛ ብር በመክፈል ቀስ በቀስ እንዲለቁ የማድረግ ስራ እየተሰራ ይገኛል ፤ ከሀረር ዋናው በር እስከ መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን የሚገኑት በግራና በቀኝ ያሉት የተለያዩ ከእስልምና ውጪ እምነት ያላቸው ሰዎች ሲሰሩበት የነበረው ቦታ በዚህ ዓይነት መንገድ እያስለቀቋቸው ይገኛል ፤ ይህን መረጃ ለማረጋገጥ ከጀጎል ውስጥ ባለፉት ሁለት ዓመታት ምን ያህል ሰው ለቆ እንደወጣ የተካሄዱትን ሽያጮች  ቢመለከቱ መልሱን ያገኙታል ፤ ሀረር ጀጎል ውስጥ ከ88 በላይ መስኪዶች ይገኛሉ ፤ ጀጎል እምብርቷ ላይ ደግሞ የመድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ይገኛል ፤ ቤተክርስትያኑ ፊት ለፊት የጨለንቆ ሰማዕታት ሃውልት ቆሞ ይመለከታሉ ፤ የሰማዕታት በዓላቸውን በሚከብሩበት ጊዜ የመድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን በቪዲዮ ቀረጻ ወቅት እንዲገባ አይፈለግም ፤ ለምን ? ብለው ቢጠይቁ …….. !!!  ???  ፤ ቢቻል ቤተክርስቲያኑን በአንድ ቀን ሜዳ ሆኖ ቢያገኙት ደስታቸው ወደር የለውም ፤ “ሐረር የመቻቻል ከተማ” የሚለው ብሂል ውስጣቸው ገብተው ሲኖሩ ግራ ይገባዎታል…፡፡ 
የክልሉ ባለስልጣናት ከሞላ ጎደል ሁሉም በሚያስብል ሁኔታ ሙስሊም ስለሆኑ በተለያዩ ጊዜያት መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ላይ የሚደርሱት በደል ይህ ነው ብሎ መጥቀስ አይቻልም ፤ የመድኃኒዓለም የዓመት ክብረ በዓል ጊዜ ውሃ እና መብራት እስከማቋረጥ ይደርሳል ፤ ሬንቦ የሚባለው የሐረር ሙዚየም ቢገቡ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ  ከሆኑ የማይነገርዎት ነገሮች አሉ ፤ ሙስሊም ከሆኑ ግን ውስጥዎ በክርስትያኖች ላይ ጥያቄ እንዲጭር በርካታ ነገሮች ይዘረዘርሎታል ፤ ከዓመታት በፊት አንድ ጊዜ ለጥምቀት የመድኃኒዓለም ታቦት ጥር 10 ወጥቶ ጥር 11 ቀን ወደ መንበሩ ለመመለስ በሰንበት ተማሪዎች ፤ በካህናትና በበርካታ ምዕመናን እየተመለሰ ሳለ ዋናውን በር ሜንጫ (የአካባቢው ጎራዴ መሳይ መሳሪያ) በያዙ በርካታ ሙስሊም ወጣቶች  በመያዝ አናስገባም አሉ ፤ ከደቂቃዎች በኋላ ግን ከሰማይ መብረቅ ወርዶ ካሉት 88 መስኪዶች ውስጥ የትልቁን መስኪድ ጨረቃና እና ኮከቧን ሲያነሳት የተመለከቱት ሰዎች በሩን መልቀቃቸው  ራሳቸው የሚናገሩት ተዓምር ነው ፤ 
ከዛሬ ሁለት ዓመት በእነዚህው ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖቻቸው አማካኝነት  የአልነጃሺን መስኪድ ከአክሱምና ከላሊበላ እኩል በአለም አቀፍ ደረጃ የማስመዝገብ ስራ መጀመራቸው ይታወቃል ፤ በጊዜው ትልቅ ተቃውሞ ያስነሳው “በኢትዮጵያ የእስልምና ሃይማኖትን የተቀበለ ንጉስ አለ” ፤ “በዓለም እስልምናን የተቀበለ የመጀመሪያው  ንጉስ የሃበሻው ንጉስ አስማን (ነጃሺ) ነው ይላሉ” ፤ “በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ የርቀት ሰላት(ሰላት አል ገይብ) የተሰገደበት ንጉስ የሃበሻው ንጉስ ነጃሺ ነው” የሚሉ ነጥቦች ናቸው ፤   የተሳሳተ የታሪክ መዛባትን የሚፈጥር መሆኑን የተገነዘቡ አይመስልም ፤ መጻህፍት ሙስሊም ንጉስ ኢትዮጵያ ላይ እንደነገሰ በጽሁፍ ተጽፎ አልተመለከትንም ፤ ታሪክን በመበረዝ የሚገኝ አንዳች አላማን ለማሳካት የሚደረግ አካሄድ እንቃወማለን ፤ ባይሆን አሁን በእኛ ዘመን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስሩ እና በምርጫው ላይ ተሳትፈው በሶስተኛ ደረጃ የተቀመጡት አቶ ሶፊያን አህመድን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የቀረቡ ሰዎችን ተመልክተናል ፤ የወደፊቱን አናውቅም ፤ እዚች ሀገር ላይ የሚኖር ሁሉም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር የመሆን እድሉ ፤ በከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ላይ ተቀምጦ ህዝብን የማስተዳደር መብቱን አንቃወምም ፤ ነገር ግን ይህን ከለላ በማድረግ የሚሰሩ ስራዎችን እንቃወማለን ፤ መተካካት የሚባለው ስትራቴጂ እምነትም መሰረት ባደረገ ሁኔታ እንዳይከናወን መንግስት የራሱን ስራ መስራት ይገባዋል፡፡ 
ይህ ክፍተት ይሞላ
በአሁኑ ሰዓት ሙስሊም ማህበረሰብ በእምነቱ ላይ ያለውን ጥያቄ ማንሳቱ ይታወቃል ፤ ህዝቡ ወክሎናል ያሉ 17 አባላቶቹን መምረጡም ይታወቃል ፤ መንግስት ለጥያቄያችሁ በቀበሌ ምርጫ ማካሄድ ትችላላችሁ የሚል መልስ መስጠቱን በመቃወም ሽብር ሲያነሱ አግኝቻቸዋለሁ ፤ ሲያስተባብሩ እና ነገር ሲጠነስሱ ነበር ያላቸውን 17ቱን ተወካዮች እስር ቤት ካስገባቸው ሳምንታት ተቆጥረዋል ፤ እነዚህ ሰዎች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ በርካታ የአላማቸው ተጋሪ ሰዎች ፍርድ ቤት አካባቢ እየተሰበሰቡ ሁኔታውን እንደሚከታተሉ እየተመለከትን እንገኛለን ፤ አሁን ይህን ጉዳይ ከመንግስት ፤ ከሃይማኖት አባቶች እና በእስር ከሚገኙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጋር በመሆን ታሳሪዎች በመንግስት ስልጣን ላይ የተቀመጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች መጅሊሱን ይቅርታ እንዲሉ እና ጉዳዩን በሰላማዊ መልክ እንዲፈታ ከፍተኛ ስራ ጀምረዋል ፤ በቅርቡም የታሰሩት ይቅርታ ጠይቀው እንደሚወጡ ምንጮች ይጠቁማሉ ፤ ይህ ሊሆን የቻለው በአሁኑ ወቅት የራሳቸው ሰዎች በመንግስት ከፍተኛ ስልጣን ላይ ስለሚገኙ ነው ፤ አሁን ወደ እኛ ስንመጣ ዋልድባ ገዳም ላይ የስኳር ልማት ሊሰራ አይገባም ካልን ወራቶች ተቆጠሩ ፤ ከመንግስት እና ከገዳሙ መነኮሳት መሃል በመሆን ነገሩን የሚያረግብ ስምምነት ላይ የሚያደርስ ባለስልጣን ግን መመልከት አልቻልንም ፤ ሁላችንም በቪኦኤ ላይ የገዳሙ አባቶች የሚናገሩትን እየሰማን ከመናደድ በቀር ምንም ያመጣነው ነገር የለም ፤ መፍትሄ ባንሻም ከድረ-ገጾች የሚጻፉትን ከማየትም አልቦዘንም ፤ የመንግስት ስልጣን ላይ ያሉ ስለ ቤተክርስቲያን ግድ የሚላቸውን ሰዎችን ማፍራት አልቻልንም ፤ በዚህ አካሄዳችን ወደ ፊት ሌሎች ስለኛ ካልመሰከሩ በቀር እኛ ስለ ራሳችን የምንናገርበት ሙግት የምንገጥምበት ጊዜ ይናፍቀናል ፤  የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሞት ሲለዩ ኢህአዴግ ሆኖ ለቦታው የሚመጥ ሰው ማየትም አልቻልንም ፤ ከላይ ካልተጠጉ ደግሞ ለትልቅ የኃላፊነት ቦታ መታጨት የማይታሰብ ነው ፤ ታዲያ እስከ መቼ ድረስ ሆድና ጀርባ ሆነን እንቀጥላለን ? ታዲያ ስለ ዋልድባ ማን ይናገር ? ፖለቲከኛ መሆን ሀጥያት ነው እንዴ ? ሙስሊሞች ለመንግስት እምነታቸውን በሚመለከት ጥያቄ ሲያነሱ  መንግስትና ጥያቄውን ያነሱት ሰዎች መካከል የራሳቸው ሰዎች ነበሯቸው ፤ እኛ ግን ለመንግስት ዋልድባን መሰረት አድርገን ጥያቄ ስናነሳ የጥያቄውን አግባብነት የሚያስረዳልን አንድም ሰው ከእኛና ከመንግስት መካከል የለንም ፤ ይህ ክፍተት ካተሞላ በቀር ወደፊት ለብዙ ችግሮቻችን መፍትሄ እንደማናመጣ እሙን ነው ፤ ወደፊትም  ይህ ክፍተት የሚሞሉ ሰዎች በቅርብ ርቀት አይታዩንም ፤ 
የወደፊት  ጫና 
አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ደቡብ ክልል በነበሩበት ጊዜ የራሳቸውን የብሔረሰብ አካላት ወደ ስልጣን የመሰብሰብ ስራ ሲሰሩ ከሲዳማ ማህበረሰብ በኩል ለምን እኛስ ? የሚል ጥያቄ መነሳቱን የቅርብ ምንጮች ይጠቁማሉ ፤ አቶ ኃ/ማርያም ለዚሀ የሰጡት መልስ “ከእናንተ የተማረ ማህበረሰብ ስለሌለ ነው ካቢኔውን በተማረ ማህበረሰብ ያዋቀርኩት” የሚል መልስ ነበር ፤ ወደፊትም ከእኛ የሚመጥን ለሚንስትርነት ደረጃ የሚበቃ ሰው መኖር አለመኖሩን ጊዜው ሲደርስ የምናየው ነገር ይሆናል ፤ ይህ ማለት በየትኛው የስልጣን ተዋረድ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ባለስልጣናት በእምነትም ሆነ በዘር አምሳያቸውን የማፈላለጋቸው ሁኔታ የማይቀር መሆኑን ነው ፤ እነዚህ ሰዎች እምነትን ወይም ብሔርን መሰረት በማድረግ ሰዎች በዙሪያቸው የሚሰበሰቡ ከሆነ አደጋው ሊከፉ ይችላል ፤ እነርሱን የሚሉ ሰዎች ጉዳዮቻቸው  በባለስልጣኖቻቸው ተጽህኖ የተነሳ በቀላሉ ሊፈቱ ይችላሉ ፤ እነዚህን ሰዎች በመተማመን ተጨማሪ የእምነት ተቋማት በሚያስፈልግም በማያስፈልጉም ቦታዎች ሊገነቡ ይችላሉ ፤ የመምረጥና የመመረጥ የመተካካት ሂደቱ እንደዚህ ባለህ የውስጥ ሴራ የሚቀጥ ከሆነ …… ቀይ መብራት ይታየናል፡፡በአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ቦታ እና የምክትሉን ቦታ የሚገኙ ሶስት ሰዎች ሲወዳደሩ አንድም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አለመኖሩ ነገን በሌላ አይን እንድናይ ያስገድደናል ፤ ካለን መረጃ ጥቂቶቹን እናንተው ዘንድ አድርሰናል ፡፡
ታቹን ስንርመጠመጥ (ለማይጠቅም ነገር ስንቦዝን) ላዩን መዘንጋት የለብንም ፤ ወደድንም ጠላንም የመንግስትን የተለያዩ  የስልጣን ተዋረዶች ላይ የተቀመጡ ሰዎች ቤተክርስትያኒቱ የምታነሳቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ቀጥተኛም ሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ተጽህኖ ሊያሳርፉ እንደሚችሉ መዘንጋት የለብንም ፤ የማንኛውም እምነት ተከታይ ከፍተኛ ባለስልጣን ሆኖ ቢሾም ተቃውሞ የለንም እኛ የምንቃወመው ከጀርባ ያለውን ስራ ብቻ ነው ፤ ይህ ህዝብና መንግስት ያሸከማቸውን ኃላፊነት ሳይዘነጉ እምነታቸውን ሳያስቀድሙ በአግባቡ የሚሰሩ ሰዎች አይመለከትም ፡፡
በመጨረሻም
ስድስት ኪሎ አፍንጮ በር ጋር ተሰርቶ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኝው ግዙፍ መስኪድ እንዴት ቦታው ሊሰጣቸው ቻለ ? ማን ጠየቀ ? ማንስ ቦታውን ፈቀደ ? የነበረውን ውጣ ውረድ እንዴት አለፉት ? ስንት ካሬ ነው ? ስንት ተከፈለበት ? ሌሎች መረጃዎች ጠቃሚ ከሆኑ ወደፊት እናቀርባለን ፤ ወደ እኛ ቤተክርስቲያን ስትመጡ ደግሞ  ቤተክህነቱ ውስጥ ጥቂት ለጥቅማቸው የቆሙ አቶ ጌታቸው ዶኒን የመሰሉ ሰዎች የባቦጋያ መድኃኒዓለምን 10 ሺህ ካሬ ታቦት ማደሪያ  ቦታ አሳልፈው ሲሸጡ እያየን ዝም ፤ በወይራ ቤተል አካባቢ የሚገኝውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የነበረውን የቦታ ይዞታ በቆርቆሮ አጥር ማጠር አቅቶን ከመንግስት ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ በመግባት የሰው ህይወት ሲያልፍ ብዙዎች ሲታሰሩ እያየን ዝም ፤ በተለያዩ በአዲስ አበባ ዳር አካባቢ የሚገኙ የቤተክርስቲያናችንን የጸበል ቦታ በፖሊስ ግብረ ኃይል መጥተው ሲያፈርሱብን ዝም ፤ዋልድባ ሲታረስ ዝም  ፤ አባቶች ሲሰደዱ ዝም ፤ ቤተክህነቱም ይሁን መንግስት በተሳሳተ ጎዳና ላይ ሲቆሙ ዝም ፤  “ዝም አይነቅዝ” የሚል የአማርኛ ብሂል የተስማማን ይመስለናል  !!!!!  ????  …… እነርሱ ደግሞ እንዴት ቦታ እንደሚገዙ ፤ እንዴት መስኪዳቸውን እንደሚተክሉ ፤ እነርሱ ሲሰሩ የባለስልጣኖቻቸው ጡንቻ ፤ እኛ ስንሰራ የባለስልጣኖቻችን ጉሸማ በንጽጽር ወደፊት እናቀርባለን  ፤ ዘምዘም ስለሚባለው በምስረታ ላይ ስለነበረ የሙስሊሞች ባንክስ ያውቃሉ ? እነማን ነበሩ አክሲዮኑን የገዙት? የትኞቹ ባለስልጣናት እና ባለሀብቶች ምን ያህል አክሲዮኖች ነበራቸው ? ለምን ተቋቋመ?  ለምንስ ፈረሰ ? ወደ ስራ ቢገባ የሚያሳድረው ተጽህኖ ምነ ነበር? (አስፈላጊ ከሆነ ብዙ አናዳጅ ነገሮች ቢኖሩም ከላይ ያነሳናቸውን ነጥቦች ወደ ፊት ከመረጃ ጋር  እናቀርባለን……)፡፡ 
ቸር ሰንብቱ…

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር