የሲዳማን የክልል ጥያቄ በማቀጣጠል ይሰሩ ከነበሩት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል ኣንዳንዶቹ ጸረ የሲዳማ ክልል ኣቋም ካላቸው ግለሰቦች ጎራ እየተቀላቀሉ መሆኑ ተሰማ



የሲዳማ የክልል ጥያቄን በተደራጀ መልኩ ለማቅረብ የብሄሩን ሽማግሌዎች በመደራጀት እና የክልል ኣስፈላጊነትን በተመለከተ ለህዝቡ በማስረዳት ከፍተኛ የሆነ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በዩኒቨርስቲ ተመሪዎች ስሰራ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ግንዛቤ የመፍጠር ኃላፊነት ወስደው በመስራት ላይ ከነበሩት ወጣቶች መካከል ኣንዳንዶቹ በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት ቡድኑን በመልቀቅ ላይ ናቸው።

ስማቸው እንድገለጽ ያልፈለጉ የሲዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ ጸረ የሲዳማ ክልል ኣቋም ያላቸው ግለሰቦች ኣንዳንድ ተማሪዎችን በገንዘብ በመደለል እና በማስፈራራት በሲዳማ የክልል ጥያቄ ላይ ያላቸውን ኣቋም እንዲቀይሩ በማድረግ ላይ ናቸው።

እነዚሁ በገንዘብ ተደልለው ጸረ የሲዳማ ክልል ኣቋም ካላቸው ቡድኖች ጎን የተቀላቀሉት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሌሎች ከዚህ ቀደም ኣብሯቸው ሲታገሉ የነበሩት በማጋለጥ እና በማሳሰር ላይ ናቸው ብለዋል።

ለኣብነትም የሲዳማን ሽማግሌዎች በማደረጀት ከፍተኝ ሚና ከተጫዎቱች ተማሪዎች መካከል ሁለቱ በቅርቡ መታሰራቸውን ኣመልከተው፤ የተቀሩትም በመፈለግ ላይ መሆናቸው ተናግረዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር