በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የተማርነውን ለህዝብና ለሀገር መስዋዕትነት የሚያስከፍለውን ጠንካራ የሥራ መንፈስ በመከተል ከሚጠበቅብን የሥራ ግዴታ በላይ አስተዋፅኦ ለማድረግ ተዘጋጅተናል ሲሉ በሲዳማ ዞን ማልጋ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ::


ነዋሪዎች እንዳሉት ድህነትን በልማት ለማሸነፍ የክቡር ጠቅላይ ሚኒሰተሩን ራዕይ በልባችን ይዘን በአዲስ የሥራ ባህል መታነፅ ጀምረናል ብለዋል፡፡
አንዳንድ አርሶ አደሮች በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስተሩ የነደፉትን የግብርና ፖሊሲና ስትራቴጂን ተከትለው ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የድካማቸው ውጤት ከትውልድ ወደ ትውልድ ተሸጋግሮ ሲታወሱ እንዲኖሩ የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡
የተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት አባቶችም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ምክንያት የደረሰብን ሀዘን የከፋ  ቢሆንም የተሰማን ቁጭት ዓላማቸውንና ራዕያቸውን ለማሳካት ብርታት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን እንደዘገበው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/29NehTextN204.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር