የጠቅላይ ሚኒስትሩን ራዕይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በጋራ ለማሳካት እንደሚሰሩ ቀዳማዊት እመቤት አዜብ መስፍን አረጋገጡ


 አዲስ አበባ ነሐሴ 27/2004 የጠቅላይ ሚኒስትሩን ዕቅድ፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በጋራ በመሆን ለማሳከት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ቀዳማዊት እመቤት አዜብ መስፍን አስታወቁ፡፡
ቀዳማዊት እመቤት አዜብ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የአስክሬን ሽኝት ስነ-ስርዓት ላይ እንደተናገሩት አቶ መለስ በህይወት ዘመናቸው ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው ጊዜ ሳይሰጡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ዕድገት የተጉ መሪ እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ህልፈተ ህይወት ከሰማበት ጊዜ አንስቶ እስከ ሥርዓተ ቀብሩ ፍፃሜ ድረስ ዝናብ፣ ብርድና ፀሃይ ሳይበግረው ኀዘኑን መግለጹ ለመሪውና ለሥራው ያለውን አክብሮት ያሳያል ብለዋል፡፡
በህይወት ዘመናቸው የሰሩት ህያው ተግባር የሚዳኛው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይናገሩ እንደነበር አስታውሰው ይኸው ዛሬ በተግባር የኢትዮጵያ ህዝብ ዳኝነቱን ሰጥቷል ብለዋል፡፡
"መለስ ለህዝብ ኖሮ ለህዝብ የሞተ ሰው ነው" በመሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሯቸውን የልማት ተግባራት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን ከግብ ለማድረስ ጥረት እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር