የሀዋሳን ሀይቅ ከጥፋት ለመታደግ ድምፃችንን እናሰማ


ዛሬ መስከረም 1 ቀን 2005 /ም ሐዋሳ የፍቅር ሀይቅና አሞራ ገደልን የመጎብኘት ዕድል አጋጥሞናል፡፡

ባለፈው ዓመት ሚያዚያ 2004 /ም የሀዋሳ ሀይቅ ጠንቅ የሆኑ ችግሮች እንዲወገዱ አስተያየት ሰንዝሬ እንደነበር ይታወቃል፡፡ነገር ግን ዘንድሮም ይሄው ተመሳሰይ ችግር ምንም ለውጥ አልታየበትም ለአብነትም ያህል በቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ መዝናኛ ካፌዎች ዘመናዊ የሚመስል የቆሻሻ ማጠራቀሚያ/Dust Bin/ አስቀምጠዋል፡፡ለኔ የገረመኝ በፍቅር ሀይቅ በኩል በእግረኛ መንገድ አካባቢ ባለ አስር ሊትር ቢጫ የዘይት ጄሪካኖች ወገባቸው ተቆርጦ ለደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚነት ተቀምጠዋል ይህ ሙከራ የማይጠላ ቢሆንም ፋይዳው ሲታሰብ ምንም የጠቀመው ነገር የለም፡፡ለምንድንው ግቢው የልማት ፅ/ቤት አለው ከተባለ ለምን ስርዓት ያለው የቆሻሻ መጣያዎችን በየቦታው ተቀምጠው አገልገሎት እንዲሰጡ የማያደርገው?በአጠቃላይ እተሰራ ያለው ስራ ሀይቁን አመጥነውም፡፡ በየሀይቁ ዳር ሶስት እና አራት በጥቅም ላይ የዋሉ የውሀ መጠጫ ላስቲኮች፣ የሲጋራና የብስኩት መቅለያዎች፣የጫት ገራባና ጋዜጣዎች በየሀይቁ ዳር ተንሳፈው ታዝቤያለሁ፡፡ አስኪ አስቡት በቀን በትንሹ 20 የውሃ መጠጫ የያዙ ሰዎች የተጠቀሙበትን ላስቲክ በሀየቁ ዳር ቢጥሉ ከበርካታ ዓመታት በኋላ አላሙራ ተራራን የሚያክል ቆሻሻ ሊፈጠር ነው ማለት ነው፡፡
ፎቶ መላኩ

ቀጥሎ ውደ አሞራ ገደል ጉዞ በእግር በማቋረጥ የተለመደውን አምስት ብር የደንቧን/የመግቢያ/ ልከፍል ለምን ስራ እንደሚውል ስጠይቅ ለልማት ስራ ነው አሉኝ፣ለየትኛው ልማት? ለአካባቢው ልማት አሉኝ አላለማችሁም ቆሻሻ እየተጣለ በትንሹ እንኳ ነገ ሀይቁ ከተበላሸ እናንተም ሰርታችሁ አትበሉም ሀዋሳም ያላት አይኗ ጠፋ ማለት ነው ስላቸው የሰለቻቸው መስላል ‘’አትድከም በአካባቢው ቋንቋ/ዳፉርቶቲ/ አሉኝ፡፡’’የአሁኑ የመግቢ ክፍያ ከባለፈው የሚለየው ደረሰኝ አለመቁረጣቸው ነው ይሄም ትዝብት ነው፣ለሰራተኞቹ የግል መተዳደሪ ነው ወይስ ህጋዊ ካርኒ መቁረት ጎጂ ባህል ሆነ፡፡
ፎቶ መላኩ
እባካችሁን አሁንም በአሞራ ገደልም ያጋጠመኝ ተመሳሳይ ነገር ነው የተለየው ነገር ቢኖር ለጫት ቃሚዎች በህግ የተፈቀደ ይመስላል ቁመቱን ያነዥረገገው ጫት ባደባባይ መግባቱና ጫቱ አስፈላጊው የምርቃና ሰርቪስ ከሰጠ በኋላ ለአሞራ ገደል የጫት ገራባቸውን፣የሲጋራ ቁራጭና ፓኬታቸውን የተጠቀለለበትን ፌስታልና የተቀዳደደ ጋዜጣቸውን ጥለውላትና ለሰጠችው አገልግሎት ችግር ሸልመዋት መሔዳቸው እጅግ አሳፋሪ ስራ በተጨባች እየተሰራ መሆኑን ስገልፅላቸሁ በታላቅ ሀዘን ነው፡፡
ፎቶ መላኩ


ሌላው እጅግ አሳፋሪው ድርጊት የአሞራ ገደል መግቢያ በር ላይ ገንዘብ የሚቀበሉ ተቆጣጣሪዎች የመንደር ህጋዊ የሰራተኛ መታወቂ ያለቸው ህግወጥ የመንደር ኪራይ ሰብሳቢዎች ወንድም ሆኑ ሴቶች በህገወጥ መንገድ አይን አውጥተው ጫት ይዘው ከሚመጡ ኮበሌዎች ለመግቢያ ከሚከፈለው 5 ብር በተጨማሪ ፈንጠር ብለው ለሚቆሙት ጠባቂ ተብዬ ጎረምሶች ብር 20 እየከፈሉ ጫታቸውን ይዘው ወደ ውስጥ መሰስ እያሉ የፍቅር መገለጫ ተብላ የምትጠራዋን ሀይቅ ፍቅር ለማሳጣትና ችግሯን ሊያባብሱባት ሲቻኮሉ ተመልክቻለሁ፡፡

ሚሊየን ብሮችን መዥረጥ አድርገው ለማውታት የማሰስቱት የሀዋሳ ከተማ ሹመኞች የሀዋሳ ሄቅን ከአደጋና ሲስተም ከሉለው አስተዳዳሪዊ አሰራር አላቆ ዘመናዊ ለማድረግ የሰራው ስራ ካለ ቢነግረንና እንም ብንተባበር እላለሁ አለበለዚያ ሀይቁን ለመታደግ በሚቀጥሉት አምስት ኣመታት ብሎ የቴሌቪዥን ካሜራ ፊት ለመቀመት የማያፍሩ መሪዎቻችን ሰርተው ያሳዩን እንላለን፡

ይህንን ስንል በሀዋሳ ከተማ ልማት የለም አላልንም ልማት በሸ ነው ነገር ግን ስለ ሀዋሳ ዕቅዳችሁም ተግባራችሁም የለም እጃችሁም አጭር ነው ለምን ቢባል ብዙ የሚመዥረጡ ብሮች ስለማያስወጣና በህዝብ ተሳትፎ በርካታ ስራዎች ስለሚሰሩ ወደ ህዝብ ወርዶ ላለመስራት የሚደረጉ ሽሽቶች አስመስሎታል፡፡

ሀዋሳ ሀይቅ በስራ ሀላፊዎች ጥረት ሳይሆን በፈጣሪ ፀጋ ያለችና ቆሻሻዋም እየጣለ ባለ ዝናብ እየተጠራረገ ገበናዋን እየሸፈነላት የምትገን ሲሆን በጋ ላይ ግን አስቡት እጅግ የሚዘገንን ነው፡፡ቤጊዜው በሚጥለው ዝናብ እየተጠራረገ የሔደው የቆሻሻ ጉድ ተመልሶ በመጣና ማንነታችንን እሲኪነግረን ባንጠብቅ፡፡
ፎቶ መላኩ

እውነት ሀዋሳ ከተማን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተጋሁ ነው እያለ በደቡብ ኤፍ ኤም ራዲዮ 100.9 MHZ እና በሬዲዮ ፋና ሻሸመኔ ቅርንጫፍ ኤፍ ኤም 103.4 MHZ እያለ ማስታወቂያና ዜና ማስነግር ብቻ ሳይሆን ብዙ እተናገሩላት ያለችውን የሀዋሳ ሀይቅ እንደ አለማያ ሀይቅ ታሪክ ሆኖ ከመቅረቱ በፊት የሀይቁን ንፅህናና ለመቆጣጠር ተንቀሳቃሽ የፅዳት ተቆጣጣሪዎችንና ለጎብኚዎች ትምህርት የሚሰጡ ሞባይል የፅዳት ሰራተኞች ቢኖሩ ትሩ ነው እላለሁ፡፡
እንዲሁም ወደ ሀይቁ የሚለቀቁ የትኛውንም ፍሳሾችና ከሀይቁ ጋር በማያያዝ ፍሳሽ በማስወገድና የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ የሚቀይሩ ማኝኛውም አይነት ህገ ወጥ አሰራሮች እንዲወገዱ ድምፃችንን በጋራ ለማሰማት ትብብር እንድናደርግና ህገወትነት እንዲወገድ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡
መላኩ አየለ 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር