ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ መልካም እድል ለሲዳማ ተማሪዎች



አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2 (ኤፍ ቢ ሲ)አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በ2005 የትምህርት ዘመን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎችን የመግቢያ ነጥብ ይፋ አደረገ፡፡

ሃገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው በ2005 የትምህርት ዘመንበከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች 116, 651 ሲሆኑ ፥ ከእነዚህም መካከል 75 ሺህ 69 (64.35%) ወንዶች እና 41,582 (35.64%)  ያክሉ ደግሞ ሴቶች ናቸው።

በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ለሁሉም መደበኛ ወንድ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥብ 294 ሲሆን ፥ ለሴት ተማሪዎች ደግሞ 290 ሆኗል።

ለታዳጊ ክልልና ለአርብቶ አደር ልጆች ወንድና ሴት ተማሪዎች 285 እና ከዚያ በላይ ሲሆን በተመሳሳይ ለግል ተፈታኞች ወንዶች 299 ለሴቶች 297 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ገልጿል።

በማኀበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ ሁሉም ለመደበኛ ተማሪ ወንዶች 275 ፥ ለሴት ተማሪዎች ደግሞ 270 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ፥ በዚሁ የትምህርት መስክ ለታዳጊ ክልልና ለአርብቶ አደር ልጆች ወንድ ተማሪዎች 270  ለሴት ተማሪዎች ደግሞ 268 እና ከዚያ በላይ ሆኗል።  መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች 270 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች ደግሞ 230 እና ከዚያ በላይ እንደሆነም ኤጀንሲው አስታወቋል።

እንዲሁም ለግል ተፈታኝ ወንድ ተማሪዎች 299 ለሴት ተማሪዎች ደግሞ 297 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ወደ ከፍተኛ ተቋማት እንዲገቡ መወሰኑን ገልጿል።

በተመሳሳይም ወደ መሰናዶ የትምህርት መስክ የመግቢያ ነጥብ ለመደበኛና ለማታ ወንድ ተማሪዎች 2.57 ሲሆን ፥ ለሴት ተማሪዎች ደግሞ 2.14 እና ከዚያ በላይ ሆኗል።  ለታዳጊ ክልልና ለአርብቶ አደር ልጆች ተማሪዎች 2.29  እንዲሁም በግል ለተፈተኑ ወንድ ተማሪዎች 2.71 ለሴት ተማሪዎች ደግሞ 2.43 መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል።  

በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ስልጠና ተቋማት ለሚሰለጥኑ ሰልጣኞች ለወንድ ተማሪዎች 2.43 ፤ ለታዳጊ ክልል ወንድ ተማሪዎች ደግሞ 2.00 ሲሆን ፥ ለሴት ተማሪዎች 2.00 እነዲሁም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ወስደው 249 እና በታች ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በደረጃ 1 እና 2 መሰልጠን ይችላሉ።


2.43 ና ከዛ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ወንዶች ፤ ከ2.00 እስከ 2.14 ያስመዘገቡ የታዳጊ ክልል ወንድ ተማሪዎች ፤ 2.00 እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች እና የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ወስደው ከ250 እስከ 275 ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በደረጃ 3 እና 4 መሰልጠን እንደሚችሉ የኤጀንሲው መግለጫ ያመለክታል።


የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ወስደው ከ276 በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በደረጃ 5 መሰልጠን እንደሚችሉ ያመለከተው መግለጫው ፥ በደረጃ 1 እና 2 እንዲሁም በደረጃ 3 እና 4 መካከል የመግቢያ ነጥብ ልዩነት ማድረግ ክልሎች አስፈላጊ ሆኖ ካገኙት በራሳቸው መወሰን እንደሚችሉ ኤጀንሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር