ጉዳዩ፡-ስለ ፍትሕ መጓደል አስቸኳይ መፍትሔ እንድሰጠን ስለማሳሰብ ይሆናል::

ቀን፡-11/01/2005
ቁጥር፡-ድሩ ቄለ01/2005 
ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞከራሲዊ ሪፓብልክ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት 
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡-ስለ ፍትሕ መጓደል አስቸኳይ መፍትሔ እንድሰጠን ስለማሳሰብ ይሆናል::
ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው በኢትዮጵያ ፌ/ዴ/ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 9 በንዑስ አንቀጽ አንድ ላይ የበላይ ህግ ያጎናፀፋቸው መብቶች በሰላማዊ አሰራር የመንግስት አካል ወይም ባለሥልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ-መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደማይኖራቸው ይደነግጋል፡፡
ይህ ህገ-መንግስት እንደገና በአንቀጽ 8 በንዑስ አንቀጽ አንድ ላይ በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉአላዊ ሥልጣን ባለቤቶች መሆናቸውን ይደነግጋል፡፡
ይሄ ሕገ-መንግሰት ከደነገገው ውጪ የደቡብ ብሔሮች በሔረሰቦችና ሕዝቦች ከልል የሚገኙ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች ለሕዝብ መልካም አስተዳደርና ልማት ማረጋገጥ ካለመቻላቸውም በላይ በሕዝብና በመንግስት መካከል አመኔታ የሚሸረሽሩ ድርጊቶችን ፣ክራይ ሰብሳብነትንና ምግባረ-ብልሹነትን ለረጅም ጊዜያት ከመፈፀማቸው ጋር ተያይዘው ሕዝቡ አንቅሮ ስለተፋቸው ይህንን ለማስለወጥ የህዝቡን ብሶት የሚቀሰቅሱ አጀንዳዎችን አንስተው በሕዝቡ መካከል በመዛት ያንኑ መልሰው ለመሸንገል በሚል አጀንዳ የመንግስትን ታአማንነት ለማግኘት ስሉ የመንግስትን ውስን ሀብት ለማባከን ላይ ታች ሲሉና የሥልጣን ዕድሜ ሲያራዝሙ ቆይተዋል፡፡
በዚህም መነሻ ህገ-መንግስቱ ለሲዳማ ህዝብ ካጎናፀፈለት መብቶች አንዱ የሆነውን ባህሉን ለማሳደግ የፍቼ-ጫምባላላ በዓል ስያከብር እስከ ዛሬ ደርሷል፡፡በነቂስ የሚወጣው ህዝብም በዝህ በዓል እንደባህሉ የሚወደውን አወድሶ፣ያልተመቻቸውንና ህጋዊነቱን ያጎደለውን ነገር ወቅሶ በሰላም ወደቤቱ ይመለሳል፡፡በነሐሴ 8-9/2004ዓ.ም የዋለው የፍቼ-ጫምባላላ በዓልም በሲዳማ ዞን አስተዳደር ጋባዥነት በዓሉን አከብሮ በዋለበት ወቅት በዴሞክራሲያዊና በጨዋ ሁኔታ ከማክበሩም በተጨማሪ እንደተለመደው ባልተመቸውና ህገ-መንግስታ መብታቸውን ነክቶብናል ያለውን ወቅሶ መንግስትን ግን አሞጋግሶ ወደየቀዬያቸው በሰላም ተመልሷል፡፡ይህ ሰላማዊነት ደግሞ የሲዳማ ባህልም ስለሆነ በነቂስ የወጣው ህዝብ በዓሉን በሰላም አከብሮ ተመልሷል፡፡ ይሁንና እነዚህ የመልካም አስተዳደር ሽታ በአጠገባቸው ያላለፋቸው መንግስትንና ህዝቡን የሚያጣላ ሥራ የሚሠሩ አመራሮች በለመዱት የአምባገነንነትና የአፈና ባህርያቸው በመጠቀም ተንኮል የወለደው (አንድ ባለሥልጣን ተሰደበ በሚል) ድርሰት በመጠቀም በሰላማዊ መንገድ መደበኛ ኑሮውን እየመራ ይህች አገር ለተያያዘቸው ልማትና እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ደፋ ቀና የሚለውን የሲዳማ ህዝብ በፍቼ-ጫምባላላ በዓል ላይ ተገኝታችሁ የክልሉን ርዕሰ መስተዳደር የሚነካ(የሚውቅስ) ሐሳብ አንፀበርቃችኋል በሚል ሰንካላ ምከንያት ህዝቡን በአጠቃላይ በማሸበር፣የገጠርና የከተማ ነዋሪዎችን ሁሉም ይተሰራል በሚል ሽብር በመንዛት ህዝቡ መንግሥት ከተያያዘው የልማት አንቅስቃሴ ጎዳና ውጪ የማድረግ ሥራ ሲሠሩ ሰንብተዋል፡፡ከማሸበርም አልፈው የሲዳማ ብሔር አባላትን ከሽማግለዎች፣ ከተማሪዎች፣ ከነጋደዎች ከመንግሥት እና ከግል ድርጅት መሥሪያ ቤት ሰራተኞች ብዙ ሰዎችን ያለህግ አካሄድ በሁሉም ወረዳዎችና በሐዋሳ ከተማ በእስር ቤት በማጎር በመደበኛ ሥራዎቻቸው በማስተጓጎል በዚህ ኑሮ ውድነት ቤተሰቦቻቸውን የመበተን አደጋ ላይ ጥለዋል፡፡ከዚህም ባሻገር ህዝቡን በከፍተኛ ምሬት ውስጥ የመክተት ሥራ እየሠሩ በመቆየታቸው የሀገር ሽማግለዎች ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንድመለሱ እና ታሣሪዎቹን እንድፈቱ ብጠይቋቸውም “እኔን 18 ሚሊዮን ህዝብ የሚያስተዳድረውን ንጉስ ስሜን በክፉ ያነሱትን እበቀላቸዋለሁ፣ገና አደሄያቸዋለሁ፣በእግሬ ሥር እስክንበረክኩ ድረስ በወኂን ቤት አወርዳቸዋለሁ” እና ወ.ዘ.ተ ብሎ እስከመዛት የለየላቸው ፍፁም አምባገነን ሆነው በማስቸገራቸው በአሁኑ ሰዓት ያለክስ ታሰረው፣ እየታሰሩና እየተሸማቀቁ የሚገኙት ለአብነት ብቻ፡- 
ተ/ቁ የታሣሪው ሥም የት/ት ደረጃ የታሣሪው ሥራ የታሠረበት ቀን የእስራት ቀናት ብዛት ክሱ ያለበት ከረጃ ምርመራ
1. አቶ እያሱ ረጋሳ MA የመንግስት ሰራተኛ አልታወቀም እስካሁን ድረስ ክስ ያልተመሰረተበት ታስረው ያሉ
2. አቶ ዱካሌ ላሚሶ MA የመንግስት ሰራተኛ 10/12/2004ዓ.ም ›› ›› ታስረው ያሉ
3. አቶ አባቴ ክሞ BSc የመንግስት ሰራተኛ 11/12/2004ዓ.ም ›› ›› ታስረው ያሉ
4. አቶ ቦሾላ ጋብሶ ቀለም ነጋዴ 19/12/2004ዓ.ም ›› ›› ታስረው ያሉ
5. አቶ አዕምሮ ወናጎ የግል ድርጅት ›› ›› ታስረው ያሉ
6. አቶ ደበበ ዳንጉራ ›› ›› ታስረው ያሉ
7.. አቶ ኡጋሞ ሀናጋ BSc መንሥታዊ ያልሆኔ ድርጅት ›› ›› ታስረው ያሉ
8. አቶ ለገሠ ሀንካርሶ 10+3 መንሥታዊ ያልሆኔ ድርጅት(NGO) 01/13/2004ዓ.ም ›› ›› ታስረው ያሉ
9 ለሎችም (1000ዎች) አልታወቀም አልታወቀም አልታወቀም አልታወቀም አልታወቀም ታስረው ያሉ
እነዚህንና ሌሎችም ሲዳማ ተወላጆች ህገ-መንግሥቱ የሠጣቸው ሰብዓዊና ዴሞክራሳዊ መብቶቻቸውን ተነፍገው በዚህ ክልል የህግ በላይነትን በመፃረር እራሳቸውን ከህግ በላይ ባደረጉ አምባገነን መሪዎች የስልክ ትዕዛዝ ብቻ ፈጽሞ ህግን በተፃረረ ሁኔታ ታጉረው የሚገኙትን ንፁሐን ዘጎች የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሳዊ መንግሰት ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስቸኳይ መፍትሔ እንድሰጣቸው ጥቆማ በመስጠት የዘግነት ግዴታችንን ለመወጣት የወደደን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ከሰላምታ ጋር
ህገ-መንግስት ይከበር!
ግልባጭ፡-
• ለኢህአዴግ ጽ/ቤት
• ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን
http://www.facebook.com/groups/289317227830513/permalink/332662266829342/

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር