የመላው ሲዳማ ሕዝብ ሕገ-መንግስታዊ ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ ትግሉ አይቆምም!!

ስማቸው እንዲገለጽ ካልፈለጉ የሲዳማ ታጋዮች የተላከ ጽሁፍ

የመላው ሲዳማ ሕዝብ ሕገ-መንግስታዊ ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ ትግሉ አይቆምም!!

ውድ የሲዳማ ሕዝብ ሆይ!
በቀደሙት ሳምንታት በሕዝባችን ላይ የተጫነውን የባርነት ቀንበር ለመታገል እንዲያስችሉ በማሰብ በርካታ መረጃ የሚያስጨብጡ ፅሑፎች ለንባብ መብቃታቸው ይታወሳል፡፡
ፅሑፎችም በይበልጥ ሕዝቡ ለነፃነቱ እንዴት መታገል እንዳለበት አቅጣጫ ከመጠቆም አልፎ የተለያዩ ወቅታዊ መረጃ የመስጠት ትልቅ ሚና ነበራቸው፡፡ የዚህ ፅሑፍ ዓላማም ከዚሁ የዘለለ አይሆንም፡፡ በዚህ መንግስት በሌለበት ሃገር ያለን ብቸኛ ሰላማዊ ትግል የማድረግ አማራጭ ስለሆነ!!
የሐዋሳን ከተማ ከሲዳማ ሕዝብ እጅ ለመቀማት (ወትሮስ የከተማዋን አብዛኛውን ክፍለ-ከተሞች ባለማወቅ ለአውሬዎች አሳልፈን ሰጥተን ነበር) የተደረገው እኩይና አስነዋሪ የደኢህዴኖች ሴራ በሲዳማና በሲዳማ ሕዝብ ወዳጆች ልብ ውስጥ ከሃምሳ በላይ ወንድሞቻችንን፣ እህቶቻችንን፣ አባቶቻችንን በጠራራ ፀሐይ ካጣንበት የዛሬ 10 ዓመት ዘግናኝ ትዕይንት በላይ የጎዳንና ዛሬም የማይቀዘቅዝ ቁጣው ነግሶ ሰንብቷል፡፡ ለነሱ ሕዝቡ ውስጥ ለውስጥ (ካድሬዎቻቸውም ጭምር) እየሰራ ያለውን ስራ እንደቀድሞው የሲዳማ ሕዝብ አንዴ ሞቅ ብሎ ከ3 ቀናት በኃላ ይቀዘቅዛል ከሚለው አዙሪታቸው ሳይወጡ አንድ ቀን በድንገት ፈንድቶ ታሪክ እንደሚለወጥና ውስጥ ለውስጥ እየሸረሸሩ የወሰዷቸውን በከተማም ሆነ ክልል ደረጃ የሚገኙ ቁልፍ ኃላፊነቶችን ተረክበንና ሕገ-መንግስታዊ መብታችንን አስከብረን በዓይናቸው የምናሳያቸው ቀን ቅርብ ነው፡፡
የጥፋት አጀንዳ አንግበው የመጡት ደኢህዴኖች ከጠበቁት በተቃራኒው የሲዳማ ሕዝብ ለነፃነቱ፣ ለአንድነቱና ለሕልውናው ታሪካዊ ትግል እንዲታገልና አንድነቱን እንዲያጠናክር ምክኒያት ሆነ፡፡ ይህም ያሰቡት የጥፋት ሴራ በብርቱ የሲዳማ ህዝብ ክንድ የከሸፈባቸው ፀረ-ሲዳማ ኃይሎች ወትሮም የለመዱትን ሲዳማን የመከፋፈል ስራ ላይ ሊጠመዱ ግድ ሆነባቸው፡፡ ከፍተኛ አመራር ከበታች አመራሮች ጋር ትንቅንቅ እንዲገጥሙ፣ ባለሃብቱን ከሕዝቡ ጋር ለማጋጨት፣ የበታች አመራሮችን ከሕዝቡ ጋር በማጋጨት፣ ምሁራንንና ተማሪዎችን ከሕዝቡ ጎን ቆሞ በአንድነት ለትግሉ እንዳይሰለፉ ያልቆፈሩት ጉድጓድ ያልፈነቀሉት ዲንጋይ የለም፡፡
ሕልውናውን ለማስከበርና ማንነቱን በንቃት ለመጠበቅ ቆርጦ የተነሳውን የሲዳማ ሕዝብ ትግል የብሔርና የዘር ግጭት ለማስመሰል ሙከራ ሲያደርጉ የከረሙ ደኢህዴኖች ይህም እንዳልተሳካላቸው ሲረዱ ሕዝቡን ለማታለል በተለያየ መንገድ ሙከራ ቢያደርጉም እንደአመጣጣቸው በብርቱ ክንድ ለሀፍረት ተዳርገዋል፡፡ ያለፈበትን ፖለቲካ ተሸክመው ለራሳቸው ተሞኝተው እኛን ለማሞኘት መቼም ወደኃላ የሚያይና የሚያስብ ጭንቅላት የተነፈጋቸው እነዚሁ የደኢህዴን ተላላኪዎች ሕዝባችንን ከፋፍለው ለማሳመንና የዘወትር የማታለል ስራቸውን ቢሞክሩም በየመድረኮቹ በሃፍረትና በውርደት ተባርረዋል፡፡ ያባረራቸው ስራቸው ነውና ሕዝቡ አይወቀስም፡፡
መቼስ ደኢህዴን በሲዳማ ሕዝብ ላይ የተለየ የጥፋት ፖሊሲ ነድፎ እንደሚንቀሳቀስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በአጠቃላይና በቅርበት ለምንከታተል ለኛ ለሲዳማዎች ግልፅ ነው፡፡ የሕዝቡን ቁጣ ለማብረድና ሕገ-መንግስታዊ የክልል ጥያቄ በሕግ አግባብ መመለስ እንዳይችል አሻፈረኝ ያለው ሰይጣናዊው ደኢህዴን "አይደለም ክልል መሆን የከተማውን አጀንዳ አላቆምንም፣ ተጠናከሮ ይቀጥላል፣ ቋቅ ቢላቸውም ሳይወዱ በግዳቸው ይውጡታል" አለ፡፡ ከፍተኛ አመራሮችን ካስፈራራና ካሳመነ በኃላ አጀንዳውን ማስፈፀም የግዴታ ግዴታ ነው በማለት ሕዝቡ ወደደም ጠላም ሐዋሳን የመቀማቱ አጀንዳ መፈፀም እንዳለበት አጥብቆ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ወትሮም ሕዝባዊ መሠረት የሌለው ደኢህዴን/ኢህአዴግ የምርጫ ወረቀት ኮሮጆ ይዞ በመሮጥና እስከ አፍንጫ በተሞላ ኮሮጆ ሕዝቡን በጥቂት ተላላኪዎቹ በአፈሙዝ በማስፈራራትና በእንጀራው በመዛት የገዛውን ድምፅ እፍረት የሌለው እንሰሳ ለዚሁ ሕዝብ መልሶ አይኑን በጨው አጥቦ "በዝረራ አሸነፍን" ብሎ ያላመነበትን ሊያሳምን ይሞክራል፡፡ ይህም አላንስ ብሎ "የሲዳማ ሕዝብ በዚህ አጀንዳ ላይ ወሳኝ አይደለም፣ ውሳኔውን ያኔ በድምፅ ሰጥቶናል፣ አሁን የሚወስነው ድርጅቱ በአባላቱ በኩል ብቻ ነው፣ ድርጅቱ በሕዝቡ እስከተመረጠ ድረስ ከተማውን በስብጥር ብቻ ሳይሆን በውጭ ዜጎችም ተክቶ ሊያሰራ ይችላል፣ ሕዝቡ በዚህ ምንም አያገባውም" ሲሉ ከትልቁ ጅብ ሽፈራው ሽጉጤ ጀምሮ እስከ ትንሹ አውሬ አለማየሁ ድረስ በዚሁ ባሳለፍነው ሳምንት አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
ሰሞኑን በሐዋሳ ከተማ በተደረጉ ስብሰባዎች ከየወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ባለስልጣናት ላይ የወረደው የስድብ ናዳ (ሕዝበኞች፣ የመስመሩን አጀንዳ ለማሳካት አቅም የሌላችሁ፣ ወዘተ)፣ ማስፈራራትና ስብዕናቸውን የሚነካ ድርጊት በመፈፀም ድርጅቱ ምን ያህል ፀረ-ሕዝብ፣ ኢ-ዴሞክራሲያዊና ሕዝባዊ መሠረት ያጣ መሆኑን ያሳያል፡፡
በሰሞኑን ውሎው ድርጅቱ የመከረባቸው አንኳር አንኳር ፀረ-ሕዝብ አጀንዳዎች መካከል፡
  1. በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት ባለስልጣናት ከሕዝብ ጎን መሰለፋቸውና አፋኙን የድርጅት ተልዕኮ አለመደገፋቸውና አለማስፈፀማቸው ከፍተኛ ጥፋት እንደሆነና ድርጅቱ አስፈላጊውን እርምጃ አጀንዳውን ባልደገፉ የሲዳማ ባለስልጣናት ላይ ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
የጥፋት አጀንዳውን የሚያራምዱና የሚደግፉ ጥቂት ሆዳም ተላላኪዎችንና የሲዳማ ጠላቶች የመንግስት ወዳጆች እንደሆኑና ለመረጣቸው ሕዝብ ሕልውና የወገኑ ኃላፊነታቸውን ጠንቅቀው ያወቁና ቃላቸውን የጠበቁ የሲዳማ ባለስልጣናት በጥፋተኝነት መፈረጃቸው ሌላው የድርጅቱን መግማትና በሕዝቡ ወደተፈለገው እራሱን በልቶ የመጥፋት ስኬት የሚወስድ ነው፡፡
  1. በየአካባቢው የሚገኙትን የሲዳማ ሞዴል አርሶ-አደሮች ሰብስበው የሃሰትና ከእውነት የራቀ ስብከት ካጠመቋቸው በኃላ ያላቸውን ማህበራዊ ጫናና ተቀባይነት ተጠቅመው የመንግስትን አፍራሽ አጀንዳ እንዲደግፉ አስገድደዋቸዋል፡፡ ሞዴል አርሶ-አደሮቹ የመንግስትን የጥፋት ሴራ በሚገባ ያልተረዱና የዘመናዊውን አስተዳደር እርከን በተገቢው ሁኔታ ያልተረዱ ከመሆናቸው የተነሳ ለማታለል ቀላል ናቸው ተብሎ መመረጣቸው ሌላው የስርዓቱ እኩይ ሴራ ማሳያ ነው፡፡ ለሞዴል አርሶ-አደሮቹ የተለያዩ ጥቅማ-ጥቅሞች በመስጠት በየደረጃው የሚነሱ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያፍኑ ለማድረግ በማሰብ የሕዝባችንን የእኩልነት ትግል የማክሸፍ ተግባር ላይ ነው ድርጅቱ የተጠመደው፡፡
ቅሉ ግን በዚህም ሆነ በዚያ በኩል የሚሰጣቸውን ምክኒያታዊ ስጦታዎችንና ጥቅማ-ጥቅሞች በማንኛውም ጊዜ ሊሰጣቸው የሚገባ መብታቸው መሆኑን የተገነዘቡ በመሆናቸው የተሰጣቸውን ተቀብለው ከነዚህ አውሬዎች ጋር የተስማሙ መስለው ቢወጡም በሕዝባዊ የሕልውና ጉዳይ ላይ ግን የማይደራደሩ መሆናቸውን እያስመሰከሩ ይገኛሉ፡፡
  1. ሰሞኑን በተደረጉ የካቢኔ ስብሰባዎች ላይ ሁለት የጥፋት ሴራ ያነገበው ሥርዓት ማሳያ የሆኑ ነጥቦች ትኩረት ተሰጥቶባቸው ነበር፡፡ የካቢኔ አባላት (ከሁሉም ወረዳዎች) ተጠርተው የሕዝቡን ህጋዊ ጥያቄ ማፈንና ማፍረስ አለመቻላቸው የአቅም ማነስ ችግር እንደሆነ ከተነገራቸው በኃላ ሁለት ምርጫ ቀርቦላቸዋል፡፡ ሁለቱም ፍፁም ጨቋኝ፣ የዴሞክራሲ መርሆዎችን ያላገናዘቡና የሲዳማ ልጆችን በሁሉም ረገድ ለማደህየት የታለመ ነው፡፡
የመጀመሪያው ምርጫ ያውን ሁኔታ ሁሉ ተጠቅሞ የክልሉን ጥያቄ ማፈንና የከተማውን የጥፋት አጀንዳ ማስፈፀም ሲሆን ሁለተኛውና ጠባቡ አማራጭ ደግሞ ይህንን ማሳካት ካልቻሉ የመንግስትን ስራ ለመልቀቅ በመስማማት በፊርማቸው እንዲያረጋግጡ የሚል ነው፡፡
ወገኖች! ይህ ምንን ያሳየናል? በዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ሕዝብ የወከለውና የመረጠው መንግስት የሚያገለግለው የሕዝብን ስሜት እንጂ የግል ጥቅምና የጥቂቶች አጀንዳ አይደለም፡፡ ቅሉ ግን እንዴት እንደተመረጡ እራሳቸው ምስክር ናቸውና ብዙ ማለት አያስፈልግም፡፡ የጥቂት አሸባሪዎች ሴራ ቢከሽፍና የሰፊው ሕዝብ ፍላጎት ቢሟላ ምን ነውር አለው? በአንባገነኖች እንኳን እኮ ተደርጎ አልፏል!! የሕዝባችን አቋም የከተማው አጀንዳው መፈፀም አይደለም ለድርድር አይቀርብም! የሕዝቡ የክልል ጥያቄም አይከሽፍም! የህዝብ አገልጋዮችም ከስራቸው አይባረሩም! Noohura Maganu Noona!!!!
  1. ሌላው ሰሞንኛ አጀንዳቸው በየአካባቢው ተሰማርተው ትግሉን በሰላማዊ መንገድ እያቀጣጠሉ ያሉ የሲዳማ ዩኒቨርሲቲ፣ የኮሌጅና በየደረጃው ያሉ ተማሪዎች እንቅስቃሴ እንዴት መግታት እንደሚቻል ማሴር ነው፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በፊት የት ወደቀ ተብሎ የማይታወቅ ተማሪን ዛሬ ሕዝባዊ ጥያቄ ይዘው ስለተነሱ ብቻ በተለያዩ የስራ መስኮች በመመደብ በስርዓቱ ክንፍ ውስጥ በመያዝ በጥቅማ-ጥቅም እንደነሱ ህልውናቸውን እንዲክዱ ማድረግ ነው፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪማ ይህንን የሞኞችን ቀልድ ከነሱ ቀድሞ የነቃ ነው፡፡ ለክልሉ ጥያቄ የደም ዋጋ ያልገበረ፣ ወንድሙን እህቱን ወላጁን ያላጣ የሲዳማ ተማሪ ካለ ያግዛቸው እስቲ!!!! ተማሪው በዴሞክራሲ አስተሳሰብ የተካነ፣ በሕግ የበላይነት ያመነ፣ ለሕዝቡ ጭምር ለእኩልነት የሚታገል እንጂ ለጥቂት ደላሎች ሽንገላ የሚታለል ቅል አዕምሮ የለውም፡፡ የራሳቸውን የአዕምሮ ቅሌት በሰው አዕምሮ ውስጥ ለመትከል መጣራቸው አያስቅም???
በመጨረሻም የተከበራችሁ የሲዳማ ነፃነት፣ እኩልነትና የጥያቄዎቻችሁ ምላሽ ናፋቂዎች!!! ከላይ በአጭሩ ለማስቀመጥ እንደተሞከረው የሕዝቡን ህልውና ለመናድና ሠላማዊ ትግልን በማፈን እኩይ ሴራ ያነገበው ደኢህዴን በተላላኪዎቹ አማካይነት ከእኩይ ተግባሩ ሊቆጠብ ባለመቻሉና የቆመውንና ለድርድር የማይበቃውን የከተማውን አጀንዳ በስውር ለማስፈፀም መጣጣር የጀመረ በመሆኑ በየወረዳው የምትገኙ ታጋዮች ጠንክራችሁ እንድትታገሉ ጥሪ እናስተላልፋለን!!
ዛሬ ካላታገልን መቼ??? እንደ ከ10 ዓመት በፊቱ አሁንም ጊዜያችሁ አሁን አይደለም እንባል ይሆንን?? እድደ ከዚህ ቀደሙ ቢንጫጩ ለሶስት ቀን ነው የተባለውን ተቀብለን ወደየቤታችን እንገባ ይሆን???
"If not now, never!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!"


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር