የፍጥጫው አካል የሆነው የመከላከያ ጄነራሎች ሹመት እንዴትና በማን ሹመቱ ተሰጠ? ጸደቀ?


የፍጥጫው አንዱ አካል የሆነው የመከላከያ ጄነራሎች ሹመት ይገኝበታል። በአንዳንድ ወገኖች የሚሰነዘር ተገቢ ጥያቄ አለ። «የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠ/ሚ/ር በሌለበት እንዴትና በማን ሹመቱ ተሰጠ? ጸደቀ?» የሚል ሲሆን፣ ለዚህ ደግሞ ከመንግስት አፈ ቀላጤዎች የሚስጠው ምላሽ ሹመቱ ቀደም ሲል በአቶ መለስ የጸደቀ እንደሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ይህ ግን ውሀ የማይቕጥር ነው ሲሉ የመከላከያ ምንጮች ማስተባበያውን ያጣጥላሉ። ምክንያቱንም ሲያስረዱ ከተሾሙት ጄነራሎች መካከል በአንጃነት ተፈርጀው የቆዩ፣ በመለስ በጥሩ አይን የማይታዩና ለረጅም አመት ለእስር የተዳረጉ እንዳሉም                              ይገልጻሉ። ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ መለስ እነዚህን  ይሾማሉ ብሎ ማሰብ ጨርሶ የማይታሰብ ነው ሲሉ ያክላሉ። እርከን ጠብቀው የተሾሙ  እንዳሉም ይጠቁማሉ። ቢሆንም ግን ህገ መንግስቱን ያልተከተለና ተገቢውን መንገድ  የልተከናወነ ሹመት እንደሆነ አልሽሽጉም።
የብ/ጄኔራል ሹመት ከሰጣቸው አንዱ ኮ/ል አ ታክልቲ በርሄ  ይገኝበታል። ከዚህም ቀደም ባቀረብኩት መጣጥፌ «መለስ ካጠፋቸው የፓርቲው አባላት» ይኸው ኮ/ል እንደሚገኝበት ጠቅሼ ነበር። በተሰነይ ግንባር ከፍተኛ ጀግንነት የፈጸመው ኮ/ል አታክልቲ  ከጦርነቱ በሁዋላ መለስን ሀይለ-ቃል በመናገሩና በማውገዙ እስር ቤት ወርዶ ለረጅም አመት ድምጹ ጠፍቶ ቆይቶአል።በ 2000 አ.ም  ከእስር ተለቆ እንደቆየና በቅርቡ የብ/ጀነራልነት ሹመት አግኝቶ በተሻለ ሀላፊነት ላይ መቀመጡ ታውቆአል።
ሌላዋ የሴት ጄነራል ተሿሚ አስካለ ብርሀኔ ትባ ላለች። ህወሀትን የተቀላቀለችው ከበርካታ ታዳጊ  እኩዮችዋ ጋር ሲሆን ጊዜው ደግሞ ግንቦት 1970 አ.ም ነበር። አብረዋት ጫካ ከገቡት ሴቶች ሁሉም ማለት ይቻላል በነመለስ ተገፍተው ሜዳ ተጥለዋል። ጀነራል አስካለ ይህን ሹመት ማግኘትዋ አስገራሚ የሚያደርገው ነጥብ አለ። የቀድሞ አየር ሀይል አዛዥ ጀ/ል አበበ (ጆቤ) ባለቤት ስትሆን ፣ጆቤን ጨምሮ የጦር አዛዦችና ከፍተወታደራዊ መኮንኖች  እንዲባረሩ የተደረገው በመለስ ህገወጥ ውሳኔና ፊርማ እንደነበር ምንጮቹ ያስታውሳሉ።
የጄ/ል አስካለ ባለቤት- እህት ከተባረሩትና ከተንገላቱት መካከል ይጠቀሳሉ። የህወሀት ፖሊት ቢሮ አመራር የነበሩት አለምሰገድ ገ/አምላክ ባለቤት ሀመልማል ተ/ሀይማኖት ስትሆን ጋዜጠኛ ሀመልማል የጄ/ል አበበ ተክለሀይማኖት እህት ናት። ከራዲዮ ፋና እና ከፓርቲው እንድትባረር የተደረገው ባለቤትዋ ከመለስ ጋር በመለያየታቸው እንዲሁም ወንድሟ በመባረሩ ነበር።
በሌላም በኩል በአንጃ ደጋፊነት ተፈርጀው ከቆዩትና በመለስ በጥሩ አይን ከማይታዩት መካከል ፍስሀ በየነ፣አብርሀም አረጋይ፣የማነ ሙሉ፣ማአሹ ሀጎስ፣ግኡሽ ጽጌና ገብሩ ገ/ሚካኤል የብ/ጀነራልነት ሹመት ካገኙት ይጠቀሳሉ።አብዛኞቹ በሎጀስቲክ መምሪያ ሲሰሩ የቆዩ ናቸው። ከዚሁሉ ጀርባ እጃቸውን አርዝመው የሹመቱን ሚና የከወኑት ስብሀት ነጋ እንደሆኑ ሲታወቅ በሁለቱ ባላንጣዎች ላይ (አዜብና በረከት)የጥፋት ሴራ ማዘጋጀቱን ገፍተውበታል።
በደብረ ዘይት የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ሹም ጄ/ል ወዲ ዳኘው በሚመራው መንግስታዊ ተቛም አቶ ቢተው በላይ ስራ መጀመራቸው ታውቛል። በመለስ ታግደውና ታስረው የነበሩት ቢተው ቁልፍ በሆነ ቢሮ መመደባቸው ሚስጥሩ ስብሀት ነጋ እንደሆኑ ተጠቁሟል። የሜ/ጄነራልነት ሹመት ካገኙት አንዱ መሀሪ ዘውዴ ሲጠቀሱ የፓርቲው አባላት «ወዲ ዘውዴ» እያሉ የሚጠሩአቸው እኚህ ጄ/ል ከትግሉ ዘመን ጀምሮ የሳሞራ ቅርብ ወዳጅ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሎአል።
በመጨረሻም በመከላከያ ቢሮ የምስራቅ እዝ ዋና እዛዥ ሆነው የቆዩት ጄ/ል ባጫ ደበሌ ባለፈው አመት በእረፍት ሰበብ ከሀላፊነት እርቀው እንዲቆዩ ከተደረገ በሁዋላ በዛው እንደተባረሩ ተገልጾላቸዋል። በአሁኑ ወቅት አሜሪካ እንዳሉ ሲታወቅ የት ከተማ እንዳሉና ለምን እንደመጡ ማወቅ አልተቻልም።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር