የእናቶችና የህፃናት ሞትን ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት አንድ አካል የሆነው የአቦላንስ አገልግሎት በክልሉ በሁሉም ወረዳዎች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡


ቢሮው  በ2ዐዐ4 በጀት ዓመት በክልሉ የሚገኙ 77 ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የምቦላንስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስቻለ ሲሆን በቀሪዎቹ 8ዐ በቀጣይ 4 ወራት ጊዜ ውስጥ የማዳረስ ስራ እንደሚሰራ በቢሮው የህክምናና ታህድሶ የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሀብታሙ ገልፀዋል፡፡
አምቦላንሶቹ ከአርግዝናና ከወሊድ ጋር በተያያዘ  የሚከሰቱ የእናቶችን ሞት ፣  በአጣዳፊ፣ በሽታዎች እንዲሁም በተለያዩ አደጋዎች የሚከሰቱ ጉዳቶችን ለመግታት ጥቅም ላይ መዋል እንዳለባቸው አመልክተዋል፡፡

የወረዳና የከተማ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ እንዳለባቸውም በመጠቆም፡፡
ይህን ተግባራዊ ለማድረግም በክልል ደረጃ  የአንቡላንስ አገልግሎት አጠቃቀምና አስተዳደር መመሪያ መውጣቱንና በሁሉም ተቋማት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚደረግ መናገራቸውን ባልደረባችን ወንድወሰን ሽመልስ ከዲላ ከተማ ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር