በመንግስት ላይ ህዝብን በማነሳሳት ተከሰው በእስር ላይ ከምገኙት የሲዳማ ተወላጆች መካከል ኣራቱ በዋስ መለቀቃቸው ተሰማ፤ የፈዴራል መንግስት የውጭ ዜግነት ላላቸው ጋዜጠኞች ጭምር ምህረት ኣድርጎ ከእስር በመፍታት ላይ ባለበት በኣሁኑ ጊዜ በርካታ ሲዳማዎች የኢትዮጵያን ኣዲስ ኣመት ታስረው እንዲያሳልፉ መደረጋቸው እንዳዛዘናቸው የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ኣስታወቁ


ከሲዳማ ኣዲስ ኣመት ከፊቼ ማዕግስት ጀምሮ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ከስራ መደባቸው እና ከመኖሪያ ቤታቸው ተይዘው ታስረው ከከረሙት ሰዎች መካከል በዛሬው እለት ኣራቱ በዋስ ተለቀዋል።

ዛሬ በዋስ የተለቀቁት ካላ ዘገዬ ሃሜሶ፤ ካላ ዘርፉ ዘውዴ፤ ካላ ጥሩነህ ቱካሌ፤ ካላ ካሳ ኦዲሶ ሲሆኑ፤ ካላ ኡጋሞን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች እንደታሰሩ ናቸው።

ታስረው ስለምገኙት ሰዎች በተመለከተ ያናገርናቸው ኣንዳንድ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት፤ የፈዴራል መንግስት የውጭ ዜግነት ላላቸው ጋዜጠኞች ጭምር ምህረት ኣድርጎ ከእስር በመፍታት በላበት በኣሁኑ ጊዜ በርካታ ሲዳማዎች የኢትዮጵያን ኣዲስ ኣመት ታስረው እንዲያሳልፉ መደረጋቸው እንዳዛዘናቸው ገልጸው፤ የምመለከታቸው የመንግስት ኣካላት የታስሩ ሰዎችን ከእስር ቤት ፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቅሏቸው ጥር ኣቅርበዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር