ፍቼ - ጨምበላላ፣ እሥራቶች፣ ሲአንና የዞኑ አስተዳደር

New
አባሎቹና ደጋፊዎቹ እንዲሁም ሌሎችም የሕብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ የሲዳማ ዞን ወረዳዎች ውስጥ እየታሠሩ እንደሚጉላሉ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አስታወቀ፤ የታሠሩት በሕገወጥ ተግባር ላይ በመሠማራታቸው ነው ሲል ዞኑ ይናገራል፡፡
በሲዳማ ዞን ሃያ አንዱም ወረዳዎች ውስጥና በሃዋሣ ከተማ በርካታ አባሎቻቸው፣ ደጋፊዎቻቸውና ሌሎችም የሕብረተሰብ ክፍሎች እየታሠሩ መሆኑን የነገሩን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ/ር ሚሊዮን ቱማቶ ናቸው፡፡

ነሐሴ 9 ቀን 2004 ዓ.ም ከተከበረው ፍቼ ተብሎ የሚታወቀው የዘመን መለወጫ በዓልና እርሱንም ተከትሎ በዋለው ጨምበላላ ባሕላዊ ጨዋታ ወቅት እንዲሁም ከዚያም በኋላ እሥራቱ መቀጠሉን የሚናገሩት አቶ ሚሊዮን የፓርቲያቸው ሰዎችና ደጋፊዎችም ሲዳማ ክልል እንዲሆንና ሃዋሣም ቻርተርድ ሜትሮፖሊታን እንድትሆን ጠይቀው እንደነበረ አቶ ሚሊዮን ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ በፍቼ በዓል ወቅት ከድርጅታቸው ሰዎች ወገን የተነሣ አንዳችም ችግር እንዳልነበረ ገልፀዋል፡፡

የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ በፍቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት የታሠሩ ሰዎች እንደነበሩና ብዙዎቹ በዋስ መለቀቃቸውን አመልክተዋል፡፡

እሥራቱ የተካሄደው ፀረ-ሠላም አድራጎት ሲፈፅሙ በነበሩ ሰዎች ላይ እንደነበረ የጠቆሙት አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ ነው በሚል ሰዎቹ የተከሰሱባቸውን ጥፋቶች ለመግለፅ አልፈቀዱም፡፡

አንድ በዞኑ ውስጥ የሚኖሩ የሲአን አባል ግን ሰዎቻቸው ሰው አክባሪና ሰላማዊም እንደነበሩ፤ በበዓሉ ወቅትም የራሣቸውን ባህል በዘፈንና በጭፈራ ከማሞገስ ያለፈ ነገር አለመፈፀማቸውን ገልፀው እንዲህ ዓይነቱ አድራጎት የድርጅታቸው ላይ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ማዋከብ አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር