የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ የድርጅቱን ሊቀመንበር እሁድና ቅዳሜ በሚያካሂደው ስብሰባ ይሰይማል

New
አዲስ አበባ መስከረም 3/2005 የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ምክር ቤት የፊታችን እሁድና ቅዳሜ አዲስ አበባ ውስጥ በማካሄድ የግንባሩ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ይሰይማል፡፡ የግንባሩ ጽህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቀው የምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መስከረም 5 እና 6 ቀን 2005 ዓ.ም ስብሰባውን በማድረግ በቅርቡ በድንገት የተለዩትን ታላቁ መሪውን የሚተካ የግንባሩ ሊቀመንበር እንዲሁም ምክትል ሊቀመንበር የሚሰይም ሲሆን ሌሎች ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። በዚሁ ወቅት በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ያካሄደውን አጭር ግምገማና የ2005 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎች የሚመለከት ሰነድ በመመርመር ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ታውቋል። ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ የ2005 ዓ.ም በድርጅትና በፖለቲካ ሥራዎች ዙሪያ መክሮ መሰረታዊ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል። ምክር ቤቱ በታላቁ መሪ በሳል አመራርና በድርጅቱ የተጀመረውን የኢትዮጵያ ህዳሴ አጠናክሮ ለማስቀጠል የድርጅቱን የአመራር ግንባታ በተመለከተ የተዘጋጀውን ሰነድ በመመርመር መሰረታዊ አቅጣጫዎችን ያመላክታል። የኢሕአዴግ ምክር ቤት ከአራቱ አባል ድርጅቶች በእኩል የተሰየሙ 180 አባላት ያሉት ሲሆን በሁለት ጉባዔዎች መካከል የግንባሩ ከፍተኛ የሥልጣን አካል ሆኖ እንደሚያገለግል የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘገባ አመልክቷል፡፡
http://www.ena.gov.et/story.aspx?ID=2439

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር