በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገቱን ሊደግፍ የሚችል የቴክኖሎጂ ሽግግርና አቅም ለመገንባት እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች ውጤት አስገኝቷል ኣቶ ደሴ ዳልኬ

አዲስ አበባ መስከረም 1/2005 በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገቱን ሊደግፍ የሚችል የቴክኖሎጂ ሽግግርና አቅም ለመገንባት እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች ውጤት እያሰገኘ መሆኑን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ገለጹ። ሚኒስትሩ አቶ ደሴ ዳልኬ ለኢዜአ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ውጤታማ የሆኑ የውጭ ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመማር የማላማድ እና የመጠቀም አቅሟም በየጊዜው እየተሻሻለ ይገኛል። 

የአገሪቱን ልማት ሊደግፍ የሚችል ውጤታማ የሆነ ቴክኖሎጂ በማፈላለግና ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ሂደት እስካሁን የተኙት ውጤቶችም አበረታች መሆናቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ሳይንስና ቴክኖሎጂ በድህነት ቅነሳና ላይ ያለውን አስተዋጽኦ በመገንዘብ ባለፉት ሁለት አመታት ዘርፉ የአገሪቱን ኢኮኖሚ የሚደግፍ እንዲሆን የተደረገው ጥረትም ስኬታማ እንደነበር ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለመሰለፍ እያደረገች ካለው ጥረት ጋር የሚጣጣም የሳይንስና ቴክኖሎጂ አቅም እንዲገነባ ልዩ ትኩረት መሰጠቱንም ሚኒስትሩ አስረድተዋል። አዳዲስ ቴክኖሎጂን የማፈላለግ የማስገባትና የመጠቀም አቅምን ለማዳበር የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓቶች በመዘርጋታቸው ቴክኖሎጂን በማዛመድ በመቅዳትና ረገድ ጥሩ ጅምሮች እየታዩ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል። 

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ በተለይ ባለፉት ሁለት አመታት ቴክሎጂን አስመስሎ በመስራት ከውጭ የሚገቡትን በአገር ውስጥ በማስቀረት ረገድ ጠንካራ አቅም እየተገነባ ነው። የአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚፈልገውን የላቀ ክህሎት ያላቸው ቴክኒሻኖች፣መሃንዲሶችና ሳይንቲስቶች ለማፍራት የሚያግዙ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋማት የማደራጀቱ ስራም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የተማሪዎች ቅበላ ከአገሪቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰው ሃይል ልማት ፍላጎት ጋር የተጣጣመ እንዲሆንና የተግባር ስልጠናውም ከማምረቻና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር እንዲቀናጅ ተደርጓል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በኢትዮጵያ ሳይንሰና ቴክኖሎጂ እንዲስፋፋ በነበራቸው ከፍተኛ ምኞች ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንደነበር ያስታወሱት ሚኒስትሩ ተማሪዎች ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ አስተሳሰባቸውን ለማሳደግ የተጀመረው ጥረትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር