የኢህአዴግ ካድሬዎች ህዝቡ ፍቅሩን ከግለሰብ ወደ ድርጅት እንዲለውጥ ጥረት እንዲያደርጉ ታዘዙ::


ኢሳት ዜና:- ሰሞኑን በመካሄድ ላይ ያለው አቶ መለስ ዜናዊን ልዩ ሰው አድርጎ የመሳል እንቅስቃሴ ድርጅቱን ስጋት ላይ እየጣለው በመምጣቱ ካድሬዎች የፕሮጋንዳ ስራቸውን ከግለሰብ ወደ ድርጅት እንዲያዞሩ ታዘዋል።
ኢህአዴግ በመጀመሪያ በአቶ መለስ ዜናዊ የግለሰብ ስብእና አስታኮ ስልጣኑን ለማደላደል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ቀይሶ የነበረ ቢሆንም፣ የፕሮፓጋንዳው እንቅስቃሴ አቅጣጫውን እየቀየረ መምጣቱ ድርጅቱን ስጋት ላይ ጥሎታል።
አቶ መለስ የሁሉም ፕሮጀክቶች አፍላቂ ፣ የኢህአዴግ ጭንቅላት ተደርገው እንዲሳሉ መደረጉ ሌሎች ሰዎች በድርጅቱ ውስጥ እንደሌሉ፣ ድርጅቱ እርሳቸው ከሌሉ ህይወት የሌለው ድርጅት ነው የሚል መልእክት እያስተላለፈ መምጣቱ ሌሎች የደርጅቱን አባላት በተለይም የህወሀት ባለስልጣኖችን  እያበሳጨ ነው።
ከሁሉም በላይ ኢህአዴግ ያለመለስ ህይወት አይኖረውም የሚለው አመለካከት በስፋት እንዲሰራጭ ያደረገው የአቶ በረከት ስምኦን የፕሮፓጋንዳ ስልት ነው በሚል ህወሀቶች ወቀሳ እያቀረቡ ነው።
ከኢህአዴግ የደህንነት ምንጮቻቸን ባገኘነው መረጃ መሰረት ግንባሩ የፕሮፓጋንዳ ስራው ከግለሰብ ወደ ድርጅት እንዲዞርና የሁሉም መስሪያቤት ሰራተኞች ለኢህአዴግ  ያላቸውን ታማኝነት መግለጥ እንዲጀምሩ መመሪያ አውርደዋል።
ኢህአዴግ እንደ ድርጅት ያደረገው አስተዋጽኦ ተረስቶ ሁሉም ነገር አቶ መለስ እንደሆኑ ተደርጎ የሚተላለፈው ቅስቀሳ፣ ድርጅቱን ሰው አልባ አድርጎ ከመሳል በተጨማሪ በድርጅቱ ውስጥ ፈላጭ ቆራጩ አንድ ሰው ብቻ እንደሆኑ ተደርጎ እንዲሳል እያደረገው ነው።
ህዝቡ አቶ መለስ ኬለለ ኢህአዴግ የለም የሚል አመለካከት እዬያዘ መምጣቱ እየተነገረ ነው። የኢህአዴግን ስርአት የሚቃወሙትም ከአቶ መለስ በሁዋላ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም መጠየቃቸው የህወሀት ባለስልጣናትን አበሳጭቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ መለስን የሚያወድሱ ህዝባዊና ሀይማኖታዊ መዝሙሮች በብዛት እየተለቀቁ ነው። አንዳንድ ድምጻዊያን አቶ መለስን ከመጽሀፍ ቅዱሱ ሙሴ ጋር እያመሳሰሉ የውዳሴ ዘፈን እየዘፈኑላቸው ነው። የመከላከያ እና ፖሊስ ሰራዊት አዛዦችና አባላት በአደባባይ ሲያለቅሱ መታየታቸው ገለልተኝነታቸውን አደጋ ውስጥ እንደጣለው አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።
የፖሊስና የመከላከያ አባላት ቢያዝኑም እንኳ  በአደባባይ ላይ መታየት አልነበረባቸው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፣ ህዝቡ ፖሊስና መከላከያ ድርውንም የአቶ መለስና የኢህአዴግ የግል ንብረት ናቸው የሚለውን አባባል ይበልጥ አጠናክሮታል።
በርካታ የወታደሮችና የፖሊስ አዛዦች “አሳዳጊያችን” እያሉ ሲያለቅሱ ታይተዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር