በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ 283 የሚሆኑ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጅ ለእረፈት የመጡ ወጣቶች የጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ላይ ማሳተፋቸውን የወረዳው ወጣቶች ጽህፈት ቤት አስታወቀ::


በጽህፈት ቤቱ ወጣቶችን የማብቃት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መኮንን ዋይሶ እንደገለፁት ለበጎ ፍቃድ አገልግሎት የተሰማሩት  ወጣቶች በችግኝ ተከላ ፣ በጤና፣ በከተማ ፅዳት ፣ በማጠናከሪያ ትምህትና በተለያዩ ዘርፎች  ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡
የወጣቶችን አቅም ለማጎልበት ጽህፈት ቤቱ  የድርሻውን እየተወጣ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጡ ከሚገኙት መካከል ደምረው ደሹሬና ታመሩ ኤልያስ የእረፍት ጊዜያቸውን ሌሎችን በሚጠቅም ተግባር ላይ ማዋላቸው እንደሚያስደስታቸው ተናግረዋል፡፡
ትምህርቱን ከሚከታተሉት ተማሪዎች መካከል ያሬድ ገነሞ ከበጎ ፈቃደኞቹ እያገኘ ያለው ትምህርት ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ውጤታማ እንደሚያደርገው መናገሩን ቁምነገር ቦጋለ ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር