የሲዳማ ፊቼ በኣል በደማቅ ሁኔታ በሃዋሳ ከተማ ተከብሮ ዋለ፤ ቁጥሩ ከመቶ ሺ በላይ ህዝብ ጉድማሌ ላይ ተገኝተዋል


በዛሬው እለት ከሃያ ኣንዱም የሲዳማ ወረዳዎች እና ከከተማ ኣስተዳደሮች የተሰባሰበው ህዝብ የሲዳማን ኣዲስ ኣመት የፊቼን በኣል በደማዊ ሁኔታ ኣክብሯል።

ከጠዋት ጀምሮ ከየወረዳዎች ወደ ሃዋሳ የተመመው ህዝብ እንደተለመደው ከተማዋን በጭፈራ ያደመቃት ሲሆን፤ ሃዋሳ የብሄሩን ባህል በሚያንጸባርቁ ልብስ ለባሾች ተሞ ልታ ውላለች።

ጉድማሌ ላይ በነበረው የበኣሉ ኣካባበር ስነ ስርኣት ላይ የተገኙት የብሄሩ ሽማግሌዎች በህላዊ መንገዱን በጠበቀ መልኩ መልካም ኣዲስ ኣመት ለመላው የሲዳማ ህዝብ የተመኝተዋል።

በደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ በበኣሉ ላይ ተገኝተው መልካም ኣዲስ ኣመት ምኞታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ በጠለፋን በሌሎች ጎጂ ባህሎች ላይ እና እንዲሁም በሌሎች ወቅታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ንግግር ለማድረግ የያዙት እቅድ ህዝቡ ባሰማው ተቃውሞ ምክንያት ሳይሳከ ቀርተዋል።

በበኣሉ ላይ የነበረው ህዝብ በወቅታዊ የሲዳማ ክልል ጥያቄ ላይ የተለያዩ መልእክቶች ፍጹም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ በጭፈራ መልክ ያስተላለፈ ሲሆን፤መልእክቶቹም በክልል ኣስፈላጊነት ላይ ያጠነጠኑ ነበሩ።

ከጉዱማሌ ላይ ተሰብሰቦ የነበረው ህዝብ በኣሉን በየቤቱ ከጎሮቤት፤ወዳጅ ዘመድ ጋር በጋራ ለማክበር ወደየቤቱ የተመለስ ሲሆን፤ ምንም ኣይነት የጸጥታ ችግር ኣለመከሰቱ ተሰምቷል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር