በሃዋሳ ከተማ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ የትራፊክ ማዕከል ግንባታ በሁለት ወር ውስጥ ተጠናቆ ስራ ይጀምራል


አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 17፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃዋሳ ከተማ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ የትራፊክ ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ ስራ ሊጀምር ነው።

በቅርቡ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ክልሎች በራሳቸው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማትን በአቅራቢያቸው ከፍተው የአሽከርካሪዎች የብቃት ማረጋገጥ አገልግሎት ማቅረብ የሚችሉበት ሁኔታ እንዲኖር አቅጣጫ አስቀምጧል።

የደቡብ ክልል ትራንስፖርት ቢሮም ይህን መሰረት በማድረግ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታውን እያካሄደ ይገኛል።

ማዕከሉ አዲስ አበባ ከሚገኘውና በሀገሪቱ ብቸኛ ከሆነው የአሽከርካሪወች ማሰልጠኛ ተቋም ጋር በአደረጃጀቱና በይዘቱ ተመሳሳይ መሆኑ ነው የተገለፀው ።

በ3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ማዕከል ለግንባታው 9.5 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገለት ሲሆን ፥ በሁለት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል።

ማዕከሉ በክልሉ ብቁ የሆኑ አሽከርካሪዎችን በማፍራቱ ሚናው  ከፍተኛ እንደሚሆን  ታምኗል ።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር