የሃዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራር፣ መምህራንና ተማሪዎች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ድንገተኛ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፀ

አዋሳ ነሐሴ 16/2004 የሃዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራር፣ መምህራንና ተማሪዎች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ ሞት የተሰማቸዉን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ፡፡
ኮሌጅ አመራር፣ መምህራንና ተማሪዎች ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጠንካራ፣ ስራ ወዳድና የዓላማ ጽናት የነበራቸዉ ቆራጥ መሪ በመሆናቸው ያቀዱት ዕቅድ ያለሙት ዓላማ ሁሉ ውጤት ሊያስገኝ ችሏል፡፡
ዜጎች በራስ በመተማመን በአብዛኛው በቴክኒክና ሙያ በመሰማራ ሥራ እየፈጠሩና ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ በተቀመጠው አቅጣጫ ብዙ ዎች ሃብትና ንብረት በማፍራት የሀገር ኩራት እስከመሆን ደርሰዋል ብለዋል ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ከድህነት እንዲላቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረት ውጤት በመሆኑ መልካም ስራቸዉ ህያዉ ሆኖ እንደሚኖር የኮሌጅ አመራር፣ መምህራንና ተማሪዎች አስታዉቀዋል ።
ታላቁ መሪያችን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለኢትዮጵያ ሀዝብ እድገትና ብልጽግና የሚበጁ መሰረቶችን የጣሉ ብሩህ አዕምሮና አርቆ አሳቢ መሪያችንን በሞት መነጠቃችን ጎድቶናል፡ ብለዋል ።
የእሳቸው ዕቅድና ስትራቴጂ ተከትለን ለአገራችን እድገትና ብልጽግና በበለጠ ጥንክረን ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን አየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጆቻቸውና ለኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን እንመኛለን ብለዋል ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር