የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በስታቲስቲክስና ማቲማቲካል ሞዴሊንግ ትምህርት የዶክትሬት ፕሮግራም ሊከፍት ነው



ሃዋሳ ነሃሴ 01/2004/የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በ2005 የትምህርት ዘመን በዶክትሬት ደረጃ የስታቲስቲክስና ማቲማቲካል ሞዴሊንግ የትምህርት ፕሮግራም ለመክፈት መዘጋጀቱን ገለጸ፡፡
ዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ቅበላ አቅሙን 30 ሺህ ለማድረስ እየሰራ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
የዩኒቨርስቲው የማቲማቲካልና ስታቲስቲክስ ትምህርት ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ ተስፉ ትላንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የትምህርት ፕሮግራሙ መከፈት ብቃት ያለው የሰው ሀይል በሚፈለገው መጠንና ጥራት ለማፍራት የላቀ አስተዋጾኦ አለው፡፡
በመሆኑም የትምህርት ፕሮግራሙ መጀመር ከዚህ በፊት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችን ወደ ውጪ በመላክ ያወጣው የነበረውን ከፍተኛ ወጭ ያስቀራል ብለዋል፡፡
ፕሮግራሙንም ለመጀመር የመማሪያ ክፍሎች፣ መምህራን፣ መጻህፍትና ለመማር ማስተማሩ ስራ የሚያስፈልጉ ሌሎች የትምህርት ግብአቶች መዘጋጀታቸውን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ወቅት በዘርፉ በሁለተኛ ድግሪ 40 ተማሪዎች ተቀብሎ በማስተማር ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር