የሀዋሳ ከነማ ስፖርት ክለብ ታሪክ


አመሠራረት


የሁለት ጊዜ የኢትዮጲያ ፕርሚየር ሊግ አሸናፊ ሀዋሳ ከነማ ስፖርት ክለብ ከኢትዮጲያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ 273 .ሜ ዕርቀት እና በ162.804 ሄክታር ቋዳ ስፋት ላይ በምትገኘው ሀዋሳ ከተማ ይገኛል፡፡ የሀዋሳ ከተማ በ1953.ም የተመሰረተች ሲሆን ከ1985.ም ጀምሮ ደግሞ የደቡብ ክልል ርዕሰ ከተማ በመሆን በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡ የደቡብ ክልል አምብርት በሆነችው ሀዋሳ ከተማ የሚገኘው የሀዋሳ ከነማ ስፖርት ክለብ የተመሰረተው በ1976 .ም ነው፡፡

የሀዋሳ ከተማ ባለፈው መንግስት ዘመን በሁለት ከፍተኞች የተከፈለች ከተማ ነበረች፡፡ በሁለቱ ከፍተኞች ስም የተቋቋሙ ሁለት ቡድኖችም ነበሩ፡፡ እነዚህ ቡድኖች ከ1968-1975 .ም ከቆዩ በሆላ በ1976 .ም ሁለቱ ቡድኖች ተዋህደው ሀዋሳ ከነማ ሊወለድ እንደቻለ ከክለቡ ፅ/ቤት ካገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሀዋሳ ከነማ ክለብ በሀዋሳ ከተማ የከተማውን ነዋሪ የሚወክል አንድ ቡድን መኖር አለበት በሚል በመዘጋጃ ቤቱ ሃላፊዎች ተነሳሽነትና በነዋሪው ጠያቂነት ሊቋቋም እንደቻለ ታውቋል፡፡ ክለቡ በተጠቀሰው ጊዜ ሲመሰረት ሀዋሳ ሐይቅ በሆላም ቀይ ኮከብ የሚባል ስያሜ እንደነበረው የክለቡ ታሪክ ማህደር ያስረዳል፡፡ የሀዋሳ ከነማ ስፖርት ክለብን ከ1976 .ም ጀምሮ በባለቤትነት እያስተዳደረ የሚገኘው የሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ነው፡፡ ይሁንና ስፖርት ክለቡ በሂደት ራሱን ችሎ መውጣት አለበት በሚል ህሳቤ ከ1996 .ም ጀምሮ አሁን ያለውን አደረጃጀት እንዲይዝ ተደርጓል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር