በሲዳማ ዞን በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በመፈጸም ላይ ያለው የሰብኣዊ መብት ረገጣና እስራት ቀጥሏል፤ ዛሬ ምሽት ላይ ሌሎች ሁለት ሰዎች ታሰሩ


በሲዳማ ዞን ውስጥ የተነሳውን ህዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ ሰዎች ህዝብ በመንግስት ላይ በማነሳሳት በምል እየታሰሩ ሲሆን፤ ሰሞኑን ታስረው ፍርድ ቤት በመቅረብ ላይ ካሉት በተጨማር ዛሬ ምሽት ላይ ካላ ጥሩነህ ቱቀላ የተባሉ በሲዳማ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የሚስሩ የሁለት ልጆች ኣባት ከበንሳ የተሰሩ ሲሆን፤ ሌላው ደግሞ  ካላ ደሳለኝ ወልደ ሚካኤል የተባሉ በዞኑ ሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ የሚሰሩ የሶስት ልጆች ኣባት ከቦና ታስረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ግለሰቦች ሃዋሳ ከተማ እና በሌሎች የዞኑ ከተሞች እና ወረዳዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በመታደን ላይ ናቸው።

ኣንዳንድ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ በላኩት መልእክት፤ የመንግስት ኃይሎች በደፈናው ሰዎችን የተለያዩ  ስሞችን እየለጠፉ በማሰር እና ሰብኣዊ መብት በመረገጥ ላይ ስለሆኑ የሚመለከተቸው የሰብኣዊ መብት ተቆርቋር ዓለም ኣቀፍ ኣካላት ጠልቃ እንዲገቡ ጥሪ ኣቅርበዋል። 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር