ልዩ ጣዕም ያላቸውን የቡና ዝርያዎች የማስተዋወቅ ሥራ ይቀጥላል


አዲስ አበባ ኢዜአ፡- የተለያየ ጣዕም ያላቸውን የኢትዮጵያ የቡና ምርቶች በዓለምአቀፍ ገበያ ደረጃ በደረጃ የማስተዋወቅ ሥራ እንደሚቀጥል የአዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ 
አርኖልድ እና ፖተር የተባለ ዓለም አቀፍ የህግ አማካሪ ድርጅት የኢትዮጵያን ጥረት በነፃ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል፡፡ 
የአዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አዴሎ በቡናው ክፍለ ኢኮኖሚ ከተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ በተደረገ የምክክር መድረክ ላይ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ልዩ ጣዕም ያላቸውን የቡና ዝርያዎችን የማስተዋወቅ ሥራ በቅርቡ ይጀመራል፡፡
ልዩ ጣዕም ያላቸውን የኢትዮጵያ የቡና ምርቶች በተለያዩ ስያሜዎች የንግድ ምልክት ፈቃድ ቀደም ሲል በሐረር፣ በሲዳማና በይርጋ ጨፌ ታዋቂ የዝርያ ምርቶች ላይ የተጀመረው ሥራ በ40 ያህል አገራትና በ113 ኩባንያዎች የባለቤትነት ዕውቅና ማግኘቱን ጠቁመዋል፡፡
ከጃፓን የቡና ምርት ተቀባይ ኩባንያዎች ጋር የነበረውን የፍርድ ክርክር የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለኢትዮጵያ በመወሰኑ በአሁኑ ወቅት ከድር ጅቶቹ ጋር የፈቃድ ስምምነት ፊርማ ተግባራዊ እንደሚደረግ ጠቁመው በህንድና በቻይናም ተመሳሳይ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን አስረ ድተዋል፡፡ 
የተለየ ጣዕም ያላቸውን የሊሙና የነቀምት የቡና ምርቶች በአውስትራሊያ የባለቤትነት ዕውቅና የሚያሰጥ የፈቃድ ስምምነት ለማድረግ ዝግጅት ተጀምሯል፡፡
በተመሳሳይም ሌሎች የኢትዮጵያ የቡና ዝርያዎችን በዓለም አቀፍ ገበያ ዕውቅና እንዲያገኙ የማስቻል ሥራ አጠናክሮ ለመቀጠል ቀደም ሲል የህግ ድጋፍ በመስጠት ከሚታወቁት የላይት ይርስ አዕምሯዊ ንብረትና አርኖልድ እና ፖተር ከመሳሳሉ የህግ አማካሪ አጋር ተቋማት ግንኙነት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
የማስተዋወቁ ሥራ እንዲቀዛቀዝ በምክንያትነት ይቀርቡ የነበሩ የሕግ ክፍተቶችን ለመሙላት መንግሥት ካለፈው ዓመት ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡
በተጓዳኝም በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላትን ያቀፈ ኮሚቴ በማዋቀር ላለፉት ስድስት ወራት ሰፊ ተግባራትን በማከናወን የማስተዋወቁን ሥራ ወደፊት ለማራመድ ጥረት መደረጉን ዳይሬ ክተሩ አመልክተዋል፡፡
የአርኖልድ እና ፖተር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ሮበርት ዊንተር በበኩላቸው የኢትዮጵያን የቡና ኢንዱስትሪ ከፈቃድ እውቅናም ባለፈ በገበያ የማስተዋወቅ ሥራ ጭምር ለማገዝ ድርጅቱ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
ይህንኑ የድርጅቱን ሁለንተናዊ እገዛ ለማግኘትና ኢትዮጵያም ከታዋቂ የቡና ምርቶቿ ተገቢውን ዋጋ ታገኝ ዘንድ የመንግሥትና የባለድርሻ አካላትን የተቀናጀ ሥራ ይጠይቃል ብለዋል፡፡
ከዚህ አንፃር ባለድርሻ አካላት በጋራ ምክክር ሥራውን በፍጥነት መጀመር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበው በዚህ በኩል ድርጅቱ የቴክኒክና አቅምን የማሳደግ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
http://www.ethpress.gov.et/ethpress/main/news.php?newsLocation=home&newsInstruction=headline&newsId=9180

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር