ዩ ኤስ ኤ ኣትላንታ የሚኖሩ የሲዳማ ዲያስፖራ ኮሚኒት ኣባላት በሲዳማ ዞን የክልል ጥያቄን ኣስመልክቶ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ ተጠናክሮ መቀጠል ኣለበት ኣሉ፤ የሲዳማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክልል ጥያቄውን የመምራት ኃላፊነት እንዲዎስዱ ጠየቁ

New

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ በኣሜሪካን ኣገር በኣትላንታ ነዋሪ የሆኑ ኣንዳንድ የሲዳማ ዳይስፖራ ኮሚኒት ኣባላት ለወራንቻ ኢፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ ከሁለት ወራት ጀምሮ  በመላዋ ሲዳማ የተቀጣጠለው የክልል ጥያቄ ማዕበል ተጠናክሮ መቀጠል ኣለበት።
መንግስት የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማ እጅ ለመንጠቅ ያደረገው ጥረት መክሸፉን ተከትሎ ጊዜ እየጠበቀ የሚነሳው የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር በጋር ማስተዳደር የሚል የክልል መንግሥት ኣመለካከት ያንገሸገሻቸው የሃዋሳ ከተማ ባለቤቶች ያነሱት የክልል ይገባኛል ጥያቄ ያለ ምንም ቅድሜ ሁኔታ መቀጠል ኣለበት ያሉት ዳያስፖራዎቹ፤ ኣዲሱ የኢትዮጵያ መንግስት ኣመራር ሀገ መንግስቱን መሰረት ባደረገ መልኩ ለህዝባዊው ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ኣለባቸው ብለዋል።
የሲዳማ ህዝብ ክልል ይገባኛል ጥያቄ  ሲያነሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ኣለመሆኑን ያስታወሱት እነኝው ኣስተያየት ሰጪዎች፤ የዛሬ ኣስር ኣመት በተመሳሳይ መልኩ የተነሳው የህዝባዊ ጥያቄ በዞኑ ምክር ቤት ኣባላት ጭምር ተቀባይነት ኣግኝቶ መቶ በመቶ ድጋፊ ለሚመለከተው ኣካል መቅረቡ ተናግረዋል።
ይሁን እና በጊዜው የሚመለከተው የመንግስት ኣካል የክልል ይገኛል ጥያቄውን በልማት እንዲቀየር ባቀረበው ኣማራጭ የክልል ጥያቄ ተደብስብሶ የታለፈ ቢሆንም በሰፊው የሲዳማ ህዝብ ልብ ውስጥ ግን ተቀብሮ  መቅረቱ ኣሁን ለሁለተኛ ጊዜ ጥያቄውን እንዲያነሳ ማገደዱን ኣስረድዋል።
በኣሁኑ ጊዜ ለሁለተኛ ጊዜ የተነሳው ክልል ይገባኛል ጥያቄ እንደከዚህ በፊት በተለያዩ ማባቢያዎች ተደብስብሶ  እንዳይቀረ ህዝቡ በመንግስት ማባቢያዎች ሳይታለል ለጥያቄ መሳከት ተግተው እንዲሰራ ኣደራ ብለዋል። 
ኣክለውም የህዝቡን ጥያቄ  ለሚመለከተው መንግስታዊ ኣካል ለማቅረብ በሽማግሌዎች ከሚያደርጉት ጥረት በተጓዳኝ በተደራጀ መልኩ ህዝቡን የመነሳሳት ስራ ሀላፊነት የሲዳማ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲረከቡ ዳይስፖራዎቹ ጠይቀዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር