የሲዳማ ዞን ካቢኔዎች የክልል ጥያቄውን ውድቅ ኣደረጉ፤ሲዳማ ለጊዜው ክልል ኣያስፈልገውም ኣሉ


ከሃያ ኣንዱም የዞኑ ወረዳዎች እና ከከተማ ኣስተዳደሮች የመጡት እነዚሁ ካቢኔዎች በወቅቱ የሲዳማ ዞን ኣንገብጋብቢ ኣጀንዳ በሆነው የሲዳማ ክልል ጥያቄ በተመለከተ ተወያይተዋል።


በውይይቱም ላይ ስለ ክልል ኣስፈላጊነት እና ካቢኔዎቹ ጥያቄውን በተመለከተ በግል በያዙት ኣቋም ላይ ሂስ እና ግሌ ሂስ ኣካህደዋል።

በግምገማው ላይ የዞኑ ካቢኔዎች የሃሳብ መለያየት የታየባቸው ሲሆን፤የክልል ጥያቄውን የምደግፉት የካቢኔ ኣባላት ኣብላጫውን ቁጥር ይዘው ነበር ተብሏል።

መድረኩን ይመሩ የነበሩት ካላ ሽፈራው ሽጉጤ  ጽኑ ጸረ ሲዳማ ክልል ኣቋም ያንጸባረቁ ሲሆን፤ የክልል ጥያቄ የመላው የሲዳማ  ህዝብ ጥያቄ ሳይሆን ከኣገሪ ውጭ የሚኖሩት የጥቂት ግለሰቦች ጥያቄ ነው በማለት ኣጣጥለዋል።


ከሂስ እና ከግሌ ሂስ ባኃላ ብዙዎቹ ሃሳባቸውን የቀየሩ ሲሆን፤ ሲዳማ ክልል ለጊዜው ኣያስፈልገውም በማለት ኣቋም ይዘዋል።

የኣጠቃላይ የግምገማውን ሁኔታ በተመለከተ የውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ በግምገማው ወቅት የካቢኔ ኣባላቱ የሲዳማን ክልል ጥያቄ እንዳይደግፉ በካላ ሽፈራው ሽጉጤ ከፍተኛ ግፊት ተደርጎባቸዋል።

ኣስተያየታቸውን የሰጡት ኣንዳንድ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች፤ የዞኑ ካቢኔዎች የሲዳማ ህዝብ ኢኮኖሚያዊ፧ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮቹን እንዲያስፈጽሙለት የመረጣቸው የገዛ ልጆቹ እስከመሆናቸው ድረስ የህዝቡን ጥያቄ በኣግባቡ የመመለስ ግደታ እያለባቸው ለምን የክልል ጥያቄ ወደጎን ልገፉት እንደወደዱ ጠይቀዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ፤ ከሁለት ሳምንት በፊት ሃዋሳ ዙሪያ ከምገኙት ማልጋ እና ወንዶ ገነት ወረዳዎች ውስጥ ተከስቶ የነበረውን ግጭት ተከትሎ ህዝቡ የክልል ጥያቄ እንዲያነሳ የማሳመን ስራ ሰርታችሃል በሚል መንግስት ግለሰቦችን እየታስረ ነው ተብሏል።

ካላ ኢያሱ ረጋሳ የተባሉት ግለሰብ የሲዳማ ክልል ኣስፈላግነት ላይ ህዝብ የማሳመን ዘመቻ ኣካህደሃል ተብሎ ታስሯል፤ በቅርቡም ወደ ፍርድ ቤት ተወስዶ ጉዳዩ እየታየ ሲሆን፤ ጉዳዩ የሚመለከተው ፍርድ ቤት ለሚቀጥለው ሳምንት እንደቀጠረው ተሰምቷል። 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር