በደቡብ ክልል በፕሬዚዳንቱና በአፈ ጉባኤዋ መካከል በተፈጠረው ውዝግብ ምክር ቤቱ ለሁለት ተከፈለ


ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ባለፈው ማክሰኞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከሲዳማ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎችን ሰብስበው “የሲዳማ ጥያቄ ፣ ወቅታዊ አለመሆኑንና አብዛኛውን ህዝብ የማይወክል መሆኑን” ተናገሩ በማለት ለማግባባት ሞክረው እንደከሸፈባቸው መዘገባችን ይታወሳል። ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ከሌሎች የመገናኛ ብዙሀን የተወከሉ ጋዜጠኞች በስፍራው ተገኝተው “የሲዳማ ጥያቄ  የጸረ ሰላም ሀይሎች ጥያቄ ነው” በማለት ይዘግባሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ ስብሰባው በውዝግብ ተደምድሟል።

ይህን ተከትሎ ፕሬዚዳንቱ የዞኑን እና የወረዳዎችን ከፍተኛ ባለስልጣናት ትናንት ሰብስበው፣ ህዝቡን የማሳመን ስራ በበቂ ሁኔታ ባመለስራታችሁ ተጠያቂዎች ናቸው ብለው ሲናገሩ፣ የዞኑ አፈ ጉባኤ የሆኑት ሴት ” የህዝቡ ጥያቄ በህገመንግስት የተቀመጠ ጥያቄ ነው ይህንን በህገመንግስት የተቀመጠ መብት፣ አይገባህም ብለን ልናሳምን አቅሙም የለንም፣ አንችልምም፣ ይህ ጥያቄ እኮ የኔም ጥያቄ ነው።” በማለት መልሰዋል።

የአፈ ጉባኤዋን መልስ ተከትሎ አብዛኛው የምክር ቤት አባላት ” እኛ ጥያቄው የህዝብ ነው፣ ከህዝብ ጋር የምንጣላበት ነገር አይኖርም ፣ ህዝቡን መብታችሁን አታስከብሩ በማለት አንቀሰቅም” በማለት በሀይለቃል መናገር በመጀመራቸው ስብሰባው ያለውጤት እንዲበተን ተደርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በዞኑ በርካታ ተነሱ የሚል ይዘት ያላቸው ወረቀቶች በብዛት እየተሰራጩ ነው። የዞኑ ባለስልጣናት እርስ በርስ መከፋፋላቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተለው ዘጋቢያችን ገልጧል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር