ኣስቂኝ ዜና ስለ ኣቶ መለስ እና የፕሬስ ነጻነት

በተለይ በላፉት ኣምስት ኣመታት የሚዲያ ነጻነት ኣፊነው ጋዜጤኞችን በየጊዜው በሰበብ ኣስባቡ ከከርቼሌ ዘብጥያ ስወረውሩ የቆዩትን መሪ ለሚዲያ ነጻነት ታግለዋል ብሎ የሚያወድስ ዜና መስማት ኣያስቂም?

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል 

-የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን

አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ብሮድ ካስት ባለስልጣን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ መሪ እንደነበሩ ገለጸ።
ባለሥልጣኑ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ የባለስልጣኑ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ጥልቅ ኀዘን እንደተሰማቸው ገልጿል። 
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያ ህዝብም መጽናናትን ተመኝቷል። 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ህገ መንግሥታዊ ዋስትና አግኝተው ተግባራዊ እንዲሆኑ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ባለሥልጣኑ ገልጿል።
በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር ማድረግ የአመለካከት እና ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለጽ መብት እውን እንዲሆን ሰርተዋል ብሏል።
አገሪቱ ከኋላ ቀርነት እና ከድህነት ተላቅቃ በአፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሟ በመልካም እንዲጠራ የሰሩ እሩቅ አሳቢና ባለዕራይ ነበሩ። ያለው የባለሥልጣኑ መግለጫ፣ እሳቸው የጀመሩትን የሰላም የልማትና የዴሞክራሲ መስመር በመከተል ለማሳካት ጠንክሮ እንደሚሰራ አረጋግጧል።
http://www.ethpress.gov.et/ethpress/main/news.php?newsLocation=home&newsInstruction=headline&newsId=9252

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር